Trendings

በማጂ ቱም ከተማ አ/ር የማጂ ከተማ የሶላር መብራት አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ነው ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በማጂ ቱም ከተማ ለዘመናት የህዝብ ጥያቄ የሆነው ይኸው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ጥያቄን ምላሽ ለመስጠት መንግስት ትኩረት በመስጠት እየሰራ ይገኛል ። ችግሮቹን ለመቅረፍ የሶላር ቁሳቁስ የያዙ አምስት የጭነት መኪናዎች ከአዲስ አበባ ተነስተው ማጂ ከተማ መድረሳቸውን የማጂ ቱም ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

Read More

ከደረጃ በታች የሚያመርቱ 14 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ

ከጥራት ደረጃ በታች ምርት በሚያመርቱ 14 ፋብሪካዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸውን ምርቶች የሚያመርቱ 100 ፋብሪካዎች ላይ የኢንስፔክሽን ስራ ተሰርቷል። በዚህም የ14 ፋብሪካ ምርቶች ከጥራት ደረጃ በታች ሆኖ በመገኘታቸው ርምጃ እንደተወሰደባቸው ተገልጿል። እርምጃ የተወሰደባቸው ፋብሪካዎች የቆርቆሮ፣ የዕቃና የልብስ ሳሙናዎች፣ የአርማታ ብረት፣ ዱቄት…

Read More

#ኢትዮጵያ_እየመከረች_ነው!

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የሚታየውን አመግባባት ለመፍታት አካታች እና አሳታፊ በሆነ መልኩ ምክክር ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ ነው። ኢትዮጵያም ይህንኑ አምናበት ሁሉም ዜጎች የሚሳተፉበት ምክክር በማድረግ ላይ ትገኛለች። እርስዎም ሀሳብዎ ለሀገራችን ችግሮች መፍትሄ እንደሚሆን አውቀው በምክክሩ በንቃት ይሳተፉ! ኮሚሽኑ በመጪው እሁድ ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሚጀምረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ የቅስቀሳና…

Read More

ትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢን ማሳደግ ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ ነዉ። አቶ አልማው ዘውዴ

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ቤቶች የውስጥ ገቢን ማሳደግ ለትምህርት ጥራት ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል ። በ2016 ዓ/ም በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር በጨታ ሙሉ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በበልግ እርሻ 141 ነጥብ 5 ኩንታል የበቆሎ ሰብል ምርት መገኘት መቻሉን…

Read More

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ተቋማት ሚናቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ተመላከተ

ኢትዮጵያ በብሪክስ ማዕቀፍ በንቃት ለመሳተፍ እና በመድረኩ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ ተቋማት የሚኖራቸውን ሚና ማጠናከር እንዳለባቸው ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ የብሪክስ የከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የቴክኒክ ኮሚቴ 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዩ የፖሊሲ አማካሪ አምባሳደር ምኒልክ ዓለሙ እንደተናገሩት፤ ጉባዔው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች አስጠብቋል። ጉባዔው የኢትዮጵያን ጥቅምና ፍላጎቶች ያስጠበቀ፣ አባል ሀገራቱ ለዓለም አቀፍ የፋይናንስ፣ የኢኮኖሚ እና…

Read More

በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ በጣለዉ ከባድ ዝናብ በተከሰተ የመሬት ናዳ አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት ህይወታቸዉ ማለፋን ፖሊስ አስታወቀ

በዞኑ አዲዮ ወረዳግራዋ ሽሽማ ቀበሌ በሌ ልማት ቡድን ተብሎ በሚጠራበት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በጣለዉ ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ የመሬት መንሸራተት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላት በመኖሪያ ቤት ዉስጥ እንዳሉ ህይወታቸዉ ማለፋን ፖሊስ ገልጿል። በአደጋዉ ሁለት መኖሪያ ቤቶች በናዳዉ መወሰዱን ያመለከተዉ ፖሊስ በአከባቢዉ የሚጥለዉ ከባድ ዝናብ የነፍስ አድኑን ስራ አስቸጋሪ አድርጎታል።

Read More

የዞኑን ልማት በማፋጠን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሁሉም ተሳትፎና ርብርብ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

ይህ የተባለው በሸካ ዞን ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ በትኩረት በሚፈፀሙ ተግባራት ላይ ያተኮረ ውይይት በቴፒ ከተማ እየተካሄደ በሚገኝበት ወቅት ነው። የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በወቅቱ እንደተናገሩት የዞኑን ልማትና እድገት ለማፋጠን እንዲሁም የዞኑን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ርብርብ ወሳኝ ነው ብለዋል። አቶ…

Read More

በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል

በዘንድሮው የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት 4 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር እንደሚሸፈን የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ወቅታዊ የግብርና መረጃዎችን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ በመኸር እርሻው 20 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት በአነስተኛ ይዞታ ባላቸው አርሶ አደሮች መልማቱን አስታውሰው፤ በሰፋፊ እርሻም ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን…

Read More

በአንደኛው ሩብ ዓመት የተገኘውን ውጤት በማስቀጠል በ2ኛው ሩብ ዓመት የላቀ አፈጻጸም ማስመዝገብ ይገባል። ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር)።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም እየተገመገመ ነው። የርዕሰ መስተዳድሩ የኢኮኖሚና መሠረተ ልማት ጉዳዮች አማካሪ ዶክተር ኢንጂነር ምትኩ በድሩ የኢኮኖሚ ዘርፍ ተቋማትን የአፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል ። ሪፖርቱን ያቀረቡት አማካሪው በነዚህ ተቋማት ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ ተጨባጭ እና ውጤታማ የሆኑ ተግባራት መከናወናቸውን በሪፖርቱ አመላክተዉ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ለይተዉ ለዉይይት አቅርበዋል።…

Read More

አመራሩ ያገኘውን ዕውቀትና ልምድ ወደተግባር በመቀየር ለህብረተሰቡ ለውጥ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።

በኮንታ ዞን “የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተጠናቋል። በማጠቃለያው መድረክ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ሰልጣኞች በነበራቸው ቆይታ በቂ ዕውቀትና ክህሎት ያገኙበት እንደሆነና የ3ኛ ዙር ስልጠና ካለፈው ዓመት ልምድ ተወስዶበት በተሻለ የቀረበበት እንደሆነ አስረድተዋል። የብልጽግና ፓርቲ…

Read More