የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ በሕግና ሥርዓት የሚመራ ምጣኔ ኃብታዊ እንቅስቃሴን ለማሣለጥ ያለመ ነው -ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)
የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ጤናማና ፍትኃዊ እንዲሁም በሕግና ሥርዓት የሚመራ ምጣኔ ኃብታዊ እንቅስቃሴን ለማሣለጥ የተዘጋጀ መሆኑን የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ገለጹ። የፍትህ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ ምንጬ ያልታወቀ ኃብት ማስመለስ፣ ማገድና መያዝን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ሥራ ላይ የዋሉት የሕግ ማዕቀፎች ወጥነት የሌላቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡ ከዚህ…
