ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ ነው
ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ተጠቃሚነቷ እንዲረጋገጥ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥናት ለመደገፍ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ። በኢንስቲትዩቱ የኤዥያና ፓሲፊክ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ጄኔራል አንተነህ ጌታቸው(ዶ/ር) በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ የጋራ ተጠቃሚነት መርህ አንዱ ነው ብለዋል። ይህንን ከግምት በማስገባት ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ብሔራዊ ጥቅምን ከማስከበር ጎን ለጎን የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው…
