በደን ተኮር የህብረተሰብ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮግራሞች በመታገዝ በማር ምርት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ደን ፣አካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ ቢሮ በደን መመናመንና መጨፍጨፍ የሚከሰቱ አማቂ ጋዞች ቅነሳ ፕሮግራም ( REED+) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በደን ተኮር ኑሮ ማሻሻያ አማራጮችና ንብ ማነብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫና የልምድ ልውውጥ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ኃላፊ…
