“ቢስት ባር” የቤንች ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል የዓለም ዓቀፍ የባህል ሀብት ሊሆን በሚችል መልኩ ባህላዊ ዕሴቱንና ይዘቱን በጠበቀ አኳኋን ለማክበር እየተሰራ መሆኑን የቤንች ሸኮ ዞን ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ::
የብሔረሰቦች በዓላት እንደ ብሔረሰቡ ማንነት፤ አሰፋፈር፣ ባህላዊ የዘመን አቆጣጠርና ወቅቶችን መሰረት በማድረግ በጋራ በመሰብሰብ ያከብራሉ፡፡በዚህም ወቅቱን የሚዋጅና እርስ በእርስ የሚያስተሳስራቸውን የጋራ አጀንዳ ይቀርፃሉ፤ ይነጋገሩበታል፤ ይወቃቀሱበታል ያለፈውን የአሁንና የወደፊቱ ታሪካቸው ዙሪያ ይወያያሉ፤ ይከራከራሉ፤ ያርማሉ፤ ያደራጃሉ፤ ያለማሉ ለቀጣዩም ትውልድ ያሸጋግራሉ፡፡በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት 13 ነባር ብሔር፣ ብሔረሰቦች ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ተዋደው፣ ተዛምደውና…
