ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ፍትህን ለሁሉም ከማድረስ ባሻገር ለመደበኛ ፍርድ ቤት ዳኞች የስራ ጫናን እየቀነሰ መሆኑ ተገለጸ
የእርቅ ተኮር ፍትህ እና የባህል ፍርድ ቤቶች ስራዎችን ለመገምገም ጀስቲስ ፎር ኦል ፒኤፍ ኢትዮጵያ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጀ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ወደ ስራ በገቡበት አካባቢ በፍትህ ተደራሽነት ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል።…
