በክልሉ የገጠር ትስስር ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና (RCFS) ፕሮግራም የስትሪንግ ኮሚቴ በሚዛን አማን ከተማ ውይይት አካሂዷል ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋጂዮ ሳፒ እንደገለፁት ክልሉ ከተቋቋመ ጥቂት ዓመታት መሆኑን ጠቁመው ከቀድሞው ክልል የተረከባቸው በርካታ የመሠረተ ልማት ዕዳዎች መኖራቸውን ተናግረዋል ። የክልሉን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የተመቻቸ ለማድረግ የመንገድ መሠረተ ልማቶችን ምቹ ሁኔታ መፍጠር የግድ በመሆኑ መንግስት አቅዶ ከሚሰራው ባሻገር…
