“ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሀሳብ ሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ መሠረት ያደረገ የቦንጋ ማዕከል ኢኮኖሚ ዘርፍ የብልጽግና ህብረት አባላት የውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ የቦንጋ ማዕከል የኢኮኖሚ ዘርፍ የብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ እና የክልሉ ቡና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የልማትና ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ኮጁአብ እንዳሉት ውይይቱ በፓርቲው ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ላይ በአመራሩ እና በአባሉ ዘንድ የጋራ አረዳድና ተግባቦት ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ገልጸዋል። ጠንካራ ፓርቲ በመገንባት ጠንካራ ሀገር መንግስት ለመፍጠር ፓርቲያችን ያስቀመጠውን ግብ ተግባራዊ…
