የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተቋማት የመረጃ ሥርዓት የዘመነ የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆን ይገባዋል፦ አቶ ታከለ ታምሩ።
በካፋ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት አመቻችነት በዞኑ የሚገኙ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች የመረጃ ሥርዓት ከማዘመን አኳያ በሚታዩ ተግዳሮቶችና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የጋራ ውይይትና ምክክር መድረክ አካሂዷል ፡፡ የካፋ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ታከለ ታምሩ በመክፈቻ ንግግራቸው የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት የመረጃ ሥርዓት የዘመነ፣ ችግር ፈቺና የህብረተሰቡን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆን ይገባቸዋል…
