አፌ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለሸኮ ብሔር የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቲካሻ ቤንጊ” የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ ለሸኮ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል “ቲካሻ ቤንጊ” የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አፌ ጉባኤው በመልዕክታቸው “ቲካሻ ቤንጊ” በክልላችን ከሚገኙ 13 ነባር ብሄረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የሸኮ ብሔረሰብ የአዲስ ዓመት ማብሰሪያ የዘመን መለወጫ በዓል እንደሆነ ተናግረዋል። በዓሉ በወርሃ ጥር በአደባባይ በጋራ የሚከበር የምስጋና…
