Trendings

በቅርቡ የኢትዮጵያን ቱባ ባህል የሚያስተዋውቅ የባህል ቡድን ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት ይጓዛል

የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ የሚገነቡ የኪነጥበብ ስራዎች በተለያዩ የዓለም ሀገራት የማቅረብ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል አሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ። ሚኒስትር ዴኤታው እንዳሉት፤ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ከፍ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት በባህልና ኪነጥበብ ዘርፎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በዚህም የኢትዮጵያን ብዝሃ ባሕልና የጥበብ ስራዎችን በማስተዋወቅ ገጽታን የመገንባት ተግባራት በስፋት መከናወናቸውን ጠቅሰዋል። ይህንንም ተከትሎ በተለይ በሰርከስ እና በስዕል ዘርፍ…

Read More

በሎስ አንጀለስ ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን ማሰር በመጀመሩ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ብሔራዊ ዘባቸውን ወደ አካባቢው አዘመቱ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ 2ሺህ የብሔራዊ ዘብ ጠባቂዎችን ወደ ሎስ አንጀለስ አሰማርተዋል። ፕሬዚዳንቱ ይህን ያደረጉት ሰነድ አልባ ነዋሪዎችን የማሰር ዘመቻን ተከትሎ ለተነሳው ተቃውሞ ምላሽ ነው። የአካባቢው ባለስልጣናት ተቃውሞውን መቋቋም ተስኗቸዋል ያሉት ፕሬዚዳንት ትራምፕ፥ የፌደራል መንግስት ችግሩን መፍታት ባለበት መንገድ ይፈታልም ብለዋል። የካሊፎርኒያ ስቴት ገዥ የሆኑት ጋቪን ኒውሶም የትራምፕ ርምጃ ውጥረቶችን እንደሚያባብስ ተናግረዋል። “ይህ የተሳሳተ ተልእኮ ነው…

Read More

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እየሳበ ነው

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እየሳበ ነው አሉ፡፡ በኢትዮጵያ እና ቤልጂየም የኢንቨስትመንት ዘርፍ ትብብር ላይ ያተኮረ የቢዝነስ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ አቶ አህመድ ሺዴ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን እየሳበ ነው ብለዋል፡፡ 10 የሚጠጉ የቤልጂየም ኩባንያዎች የተሳተፉበት የልምድ ልውውጥ መድረክ የዚህ ፍላጎት አካል መሆኑን…

Read More

ከዓመታት አዙሪት መውጣት ያልቻልነው ችግሮቻችንን በውይይት መፍታት ባለመቻላችን ነው፡- ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

ከዓመታት አዙሪት መውጣት ያልቻልነው ችግሮቻችንን በውይይት መፍታት ባለመቻላችን ነው ሲሉ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል፡፡ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን የፌደራል ባለድርሻ አካላት የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መድረክ ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር መስፍን፣ የእድሜ ጠገብ ባለታሪክ የሆነችው ኢትዮጵያ በብዙ ውጣውረድ ውስጥ ማለፏን ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ የገጠሟን ችግሮች ለመፍታት ህዝቡን በማሳተፍ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በፓሪስ የሚገኘውን የኖትረዳም ካቴድራል ጎበኙ

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ጉብኝቱ የቅርሱ መጠበቅን ባሕላዊ እና አለም አቀፍ ዋጋ ያመላከተ ነበር። እ.ኤ.አ በ2019 ከተከሰተው የእሳት አደጋ በኋላ የተደረጉ የጥበቃ ሥራዎች ፈረንሳይ ለታሪካዊ ምልክቶቿ ጠብቃ ለመጪ ትውልዶች ለማቆየት ያላትን ፅኑ አቋም የሚያሳዩ ናቸው ሲልም ገልጿል። ጉብኝቱ ለኢትዮጵያ ትርጉም ያለው ትምሕርት የሰጠ መሆኑን ጠቁሞ ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እስከ ጎንደር ፋሲለደስ እስከ አባጅፋር…

Read More

በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ከ300 በላይ ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል – የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ60 በላይ ከተሞች ላይ እየተከናወነ ባለው የኮሪደር ልማት ከ300 በላይ ፕሮጀክቶች በመጀመሪያው ዙር መጠናቀቃቸውን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ። የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከተሞች ተመራጭ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንዲሆኑ ታቅዶ እየተተገበረ የሚገኝ የልማት ፕሮግራም ነው፡፡ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከናወነውን የኮሪደር ልማት ስራዎች አስመልክቶ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ ከኢዜአ ጋር ቆይታ…

Read More

ዘመኑን የዋጀው ዲጂታል አገልግሎት

በኢትዮጵያ የሚገኙ በርካታ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከጊዜ ወደ ጊዜ አቅማቸውን በማጎልበት ዲጂታል አሰራርን ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛል። የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማትም ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆኑ የዲጂታል አገልግሎቶችን በማቅረብ የበርካቶች ጊዜና ጉልበት መቆጠብ ችለዋል። በጉዳዩ ላይ የኢኖቬሽንናቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ይሽሩን አለማየሁ (ዶ/ር) እና በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ክፍል መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ፈጠነች መስቀሌ…

Read More

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ወጣቶች እና ማህበረሰብ

አዲስ የዕድል በር ተከፍቷል — www.ethiocoders.et የወደፊቷ ኢትዮጵያን የድጅታል አካል እንድትሆኑ የሚያግዙ የነጻ የመስመር ላይ ኮርሶችን እየሰጠ ነው። የምትኖረው በከተማ ወይም በገጠር ይሁን አሁን የመማር እና የማደግ እድል አለህ፡- አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የውሂብ ትንተና የዳታ ፕሮግራም አንድሮይድ ልማት ተማሪዎች፣ የተመራቂዎች፣ የመንግስት ሠራተኞችና ስራ ፈላጊዎችን ለመማርማር ህልም ያላቸውን እንጠይቃለን። አብረን እንነሳ። ዲጂታል ክህሎቶችን ይማሩ። የኮምፒውተር እውቀት ያለው…

Read More

አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ተባለ

በኢትዮጵያ አዳዲስ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ወደ ስራ መግባታቸው በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለተሰማሩ አልሚዎች ምቹ አጋጣሚ እየፈጠረ መሆኑን ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ። ፕሬዚዳንት ታዬ በድሬዳዋ ከተማ የተገነባውን የፓዮኔር ሲሚንቶ ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ማስፋፊያ ፕሮጀክት መርቀዋል። በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ እና በቻይና ባለሃብቶች አጋርነት የተገነባው ፓዮኔር ሲሚንቶ ፋብሪካ ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ዕድገት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አለው።…

Read More

የሌማት ትሩፋት ለማር ምርታማነት እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ ለማጠናከር እየተሠራ ነው

በሀገሪቱ ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። “ንቦችን እንጠብቅ” በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፍ የንብ ቀን እና 2ኛው ዘላቂ የንብ ማነብና እጽዋት ተራክቦ ኮንፈረንስ በጅማ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡ በዚሁ ወቅት አቶ አደም በሀገሪቱ የምግብ…

Read More