Trendings

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በሁሉም አመላካቾች የሚጠበቅበትን ውጤቶች እያስመዘገበ ይገኛል – የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በሁሉም አመላካቾች የሚጠበቅበትን ውጤቶች እያስመዘገበ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አፈጻጸም ጉዳዮችን አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማስመዝገብ በሚያስችል አበረታች ሂደት ማሳካቱን አንስተዋል፡፡ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ከተያዘለት የገቢ ማሳደግ፣ የዕዳ ሽግሽግ፣…

Read More

ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤን ማዘጋጀቷ ለዘርፉ የሰጠችውን ትኩረት ያሳያል፦ የዓለም የጤና ድርጅት

ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ የጤና ኢኖቬሽን እና ጥራት ጉባኤን በአድዋ ድል መታሲያ እያስተናገደች ትገኛለች። የዓለም የጤና ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶ/ር ኦውን ካሉዋ በጉባኤው፥ የጤናው ዘርፍ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን እንዲያቅፍ እና በአባል ሀገራት የጤና ፍትሃዊ ተደራሽነት እንዲረጋገጥ ድጋፍ በማደረግ ላይ ይገኛል ብለዋል። በትብብር ከተሠራ ምንም የማይቻል ነገር የለም ያሉት ተወካዩ፤ በየጊዜው የሚያጋጥም ወረርሽ…

Read More

የኮንስትራክሽን ዘርፉን ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ ነው – ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ

የኮንስትራክሽን ዘርፉን ይበልጥ ለማሳደግና ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ ነው አሉ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፡፡ ዓለም አቀፍ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ እና የምስራቅ አፍሪካ መሰረተ ልማት ኤክስፖ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ መካሄድ ይጀምራል፡፡ ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት÷ ኮንስትራክሽን የአንድ ሀገር እድገት በትክክለኛ መንገድ ላይ እንደሚገኝና ኢኮኖሚው እያደገ መምጣቱን የሚያመላክት ነው፡፡ ዘርፉ ለኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር…

Read More

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የሚሰራው ስራ ሊጠናከር ይገባል፡- የሰላም ሚኒስቴር

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና አንድነትን ለማጠናከር የሚሰራው ስራ ሊጠናከር እንደሚገባ የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ ተናግረዋል። ሀገር አቀፍ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ የጎሳ መሪዎች እና የሰላም ተቋማት አመራሮች የምክክር መድረክ በአፍሪካ የአመራር ልህቀት ማዕከል እየተካሄደ ነው። በምክክር መድረኩ የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ ኢትዮጵያ በርካታ የከበረና የዳበረ ባሕላዊ የሰላም ሐብቶች ያሏት ሀገር መሆኗን ገልጸዋል። እነዚህ ሐብቶች ግጭቶችን…

Read More

ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኃይል ግንኙነት የመሪነቱን ሚና እየተጫወተች ነው – ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ ለቀጣናዊ የኃይል ግንኙነት የመሪነቱን ሚና እየተጫወተች መሆኑን ገለጹ። የውጭ ጉዳይ ሚነስትሩ ይህን ያሉት፤ በአዲስ አበባ መካሄዱን በጀመረው አራተኛው የናይል ውኃ ምክንያታዊና ፍትሐዊ አጠቃቅም ጉባዔ /አፍሪራን/ ላይ ነው።ጉባዔው ቀጣናዊ የኃይል ግንኙነት ለሁሉም እና ለዘላቂ ልማት በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተደረገ የሚገኘው።የኃይል ግንኙነት የተመድ 2030 እና የአፍሪካ 2063 የልማት ግቦችን…

Read More

የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ለህዝብ ክፍት ሆነ

እድሳት ተደርጎለት ላለፉት 4 ወራት በሙከራ ስራ ላይ የቆየው የብሔራዊ ቤተመንግስት ሙዚየም ከዛሬ ጀምሮ ለህዝብ ክፍት ተደርጓል፡፡ ቤተመንግስቱ ጥንታዊ ተሽከርካሪዎችና መካነ እንስሳትን ጨምሮ በውስጡ በርካታ ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘ ሲሆን፥ ደረጃቸውን የጠበቁ ሬስቶራንቶችና ስፓዎች ይገኙበታል፡፡ ሙዚየሙ ክፍት መደረጉን አስመልክተው የብሔራዊ ቤተመንግስት ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምትኩ ደሬሳ በሰጡት መግለጫ፥ ቤተመንግስቱ ኢትዮጵያን ከተረጂነት ለማላቀቅ ትልቅ ሚና እንዳለው አንስተዋል፡፡…

Read More

ታዋቂ አርቲስቶችና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመመልከት ኮንታ ዞን ደርሰዋል

በሀገር ደረጃ ለ3 ተከታታይ ቀናት ከኪነጥበብ ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጎ እንደ ሀገር እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ምልከታ ለማድረግ እንደሆነ ለማድረ ያለመ መሆኑን የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ብላቴ ገልጸዋል። ባለሙያዎቹ ወደ ኮንታ ዞን ኮንታ ኮይሻ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በአቀባበል ወቅት የዞን አመራር አካላትና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል። ባለሙያዎቹ በቆይታቸው…

Read More

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት የተገለጠበት ብሔራዊ ሀብታችን ነው፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አባቶቻችን ኪሳቸውን ፈትሸው፣ እናቶቻችን መቀነታቸውን ፈትተው ጥሪት ያፈሰሱበት እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት አባላት መስዋዕት የሆኑለት ብሔራዊ ሀብታችን ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ። የሕዳሴ ኮር ሦስተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል “ሕዳሴን በሕዳሴ ኮር” በሚል መሪ ሐሳብ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ…

Read More

የውጭ ዜጎች የቋሚ ንብረት ባለቤትነት ረቂቅ አዋጅ ቢጸድቅ የሚያስገኘው ጠቀሜታ ምንድን ነው?

65 ዓመታትን የስቆጠረውንና የውጭ ዜጎች የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለይዞታ መሆን እንዳይችሉ ያደረገውን አዋጅ ለማሻሻል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ይታወቃል። በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ውይይት እያካሄደ ነው። የፍሕ ሚኒስቴር እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል። አዋጁ መሻሻሉ ስለሚኖረው ጠቀሜታ…

Read More

ኢትዮጵያ በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔዎችን እየሰጠች ትገኛለች – ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር)

ኢትዮጵያ በዲጂታል ስርዓት የታገዘ የግምገማ ስርዓትን በመከተል በመረጃ ላይ የተመሰረተ የፖሊሲ ውሳኔዎችን እየሰጠች እንደምትገኝ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) ተናገሩ። የአፍሪካ የግምገማ ማህበር 25ኛ የምስረታ በዓሉን ምክንያት ያደረገ ውይይት በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ኢትዮጵያ ለምትተገብራቸው ፖሊሲዎችና የልማት ዕቅዶች ውጤታማነት ጠንካራ የግምገማ ስርዓት ዘርግታ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።…

Read More