በጋምቤላ ክልል ከወዳደቁ ፕላስቲኮች ነዳጅ ማምረት የቻለው ግለሰብ
በጋምቤላ ክልል አኙዋ ዞን ጎግ ወረዳ የሚኖረው አቶ ኡጁሉ ኡሞድ የወዳደቁ ፕላስቲክ እቃዎችን እና ፌስታሎችን በመሰብሰብ የቤንዚን እና የናፍታ ነዳጅ ማምረት ችሏል። የወዳደቁ ፕላስቲኮችን እና ፌስታሎችን ሲሰበስብ ሰዎች እንደ እብድ ይቆጥሩት እንደነበር የገለጸው አቶ ኡጁሉ፤ የወዳደቁ የፕላስቲክ እቃዎችና ፌስታሎችን በመሰብሰብ የቤንዚንና ናፍታ ነዳጅ በመስራት ውጤታማ መሆኑን ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የነዳጅ ምርቱ በጀነሬተር እና በሞተር ሳይክል…
