Trendings

በ2018 ዓ.ም የብልፅግና ፓርቲን ወክለው የማረቃ ገና ምርጫ ክልል እጩዎች ይፋ ሆኗል

በ2018 ዓ.ም ለሚካሄደው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ እጩዎች ይፋ ተደርገዋልደ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ (የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት) #የክልል ም/ቤት ማረቃ ገና ምርጫ ክልል ተወካዮች 1- ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋገሾ ለክልል ምክር ቤት። 2- አቶ እስራኤል አታሮ ለክልል ምክር ቤት 3-አቶ ታርኩ አካሉ ለክልል ምክር ቤት 4-አቶ ደረሰ ገትሳ ለክልል ምክር ቤት 5-አቶ…

Read More

የኢትዮጵያን የሰላም ጥረት ማገዝና መደገፍ የቀጣናውን ሰላም የማጽናት ስራ ነው – አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ

የኢትዮጵያን የሰላም ጥረት ማገዝና መደገፍ የቀጣናውን ሰላም የማጽናት ስራ መሆኑን በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ገለጹ። የአፍሪካ አህጉራዊ የሰላም ኮንፍረንስ “የበለፀገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ በአፍሪካ የዘላቂ የልማት ግቦችን ለማሳካት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ማስፈን…

Read More

የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ዜጎች ላይ ሊፈጥር የሚችለውን ጫና ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፎርሙ እጅ አጠር ዜጎችን የሚጎዳ እንዳይሆን ከፍተኛ የድጎማ በጀት መያዙን አስታውቀዋል፡፡ ከደመወዝ ጭማሪ ጋር የተያያዙ የመረጃ ክፍቶችን በማጥራት ማሻሻያው ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግም ጠቁመዋል፡፡ የዋጋ ግሽበት የዓለም ሀገራትን በተለያየ ደረጃ እየፈተነ እንደሚገኝ…

Read More

አፍሪካዊያን የጋራ ብልጽግናቸውን የሚያረጋግጥ የትምህርት ሥርዓት መገንባት ይጠበቅባቸዋል

አፍሪካዊያን የጋራ ብልጽግናቸውን የሚያረጋግጥ የትምህርት ሥርዓት መገንባት ይጠበቅባቸዋል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አፍሪካዊያን የጋራ ብልጽግናቸውን የሚያረጋግጥ የትምህርት ሥርዓት መገንባት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ። 41ኛው የአፍሪካ የትምህርት ምዘና ዓመታዊ ጉባዔ የትምህርት ምዘናን ለማሸጋገር ጥራት ያለው ትምህርትና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው። ጉባዔው መጻኢ ዕድላችንን ለመወሰንና የተማረ…

Read More

ከምርጫ ስራዎች ጎን ለጎን ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትን በማስተሳሰር አመራሩ በቁርጠኝነት ውጤታማ ስራ መስራት አለበት ፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

የደቡብ ምዕራብ ክልል ምክትል ር/መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የካፋ ዞን ጊምቦ፣አዲዮና ቦንጋ ከተማ መዋቅሮች ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትና የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዝግጅት አፈጻጸም ገምግሟል ። ከምርጫ ስራዎች ጎን ለጎን ወቅታዊ የኢኒሼቲቭ ተግባራትን በማስተሳሰር አመራሩ በቁርጠኝነት ውጤታማ ስራ መስራት እንዳለበት የተናገሩት አቶ ማስረሻ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅና የመንግስት ልማት…

Read More

የጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) የሩዋንዳ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው: – ቢልለኔ ስዩም

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሩዋንዳ ጉብኝት ኢትዮጵያ ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ፡፡ ቢልለኔ ስዩም የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸውን የሩዋንዳ ኪጋሊ የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም ፥ ጉብኝቱ በሁለት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን አንስተዋል፡፡ አንደኛው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፖል…

Read More

አስፈጻሚ ተቋማት የዞኑን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በሚያስችሉ ተግባራት ላይ እንዲያተኩሩ ተጠየቀ።

የሸካ ዞን ምክርቤት የዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ በስሩ የሚከታተላቸዉን የአስፈጻሚ አካላት የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ገምግሟል ። መድረኩን የመሩት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ በወቅቱ እንደገለጹት በግማሽ ዓመቱ የታዩትን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም በህብረሰቡ ተጠቃሚነት ላይ በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። ዋና አስተዳዳሪው ከግብዓት ገንዘብ አሰባሰብ ጋር…

Read More

የወረዳ የማህበረሰብ ወኪሎች በአጀንዳዎቻቸው ላይ እየተወያዩ ነው፡፡

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የማህበረሰብ ወኪሎች ከትላንት ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም ከሰዓት ጀምረው ከወከሉት ማህበረሰብ ይዘዋቸው የመጡ አጀንዳዎችን በውይይት በማደራጀት ላይ ናቸው፡፡ በዚህ የምክክር መድረክ ከ57 የክልሉ ወረዳዎች የተወጣጡ 1003 የሚሆኑ የዘጠኝ የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎች በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡ እነዚህ የወረዳ የማህረሰብ ክፍል ወኪሎች ምክክራቸውን እስከ ነገ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም ድረስ…

Read More

ኮሚሽኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አጀንዳዎችን ተረከበ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሰባት ክፍሎችና በ64 ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ያዘጋጃቸውን አጀንዳዎች መረከቡን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ አጀንዳዎቹን የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር) ከሌሎች ኮሚሽነሮች ጋር በጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሰለሞን አየለ ከተመራው የምክር ቤቱ የሥራ አስፈፃሚ አባላት ቡድን መረከባቸው ተገልጿል፡፡ መስፍን (ፕ/ር) በዚሁ ወቅት ኮሚሽኑ ከምክር ቤቱ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሞ…

Read More

ፓርቲያችን ብልጽግና ባሳለፍናቸው አመታት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮር ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱ ተገለፀ

በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት “ከቃል እስከ ባህል “በሚል መሪ ቃል 2ኛውን የብልጽግና ፓርቲ መደበኛ ቅድመ ጉባኤ የማጠቃለያ ኮንፈረንስ በጀሙ ከተማ አካሂደዋል። ጉባኤው በተለያዩ የባህላዊ ዉዝዋዜ የታጀበ መሆኑ ተጠቅሷል። በኮንፍረንሱ መልእክታቸውን ያስተላለፉት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸዉ ኬኒ ፓርቲያችን ብልጽግና በባለፉት አመታት በርካታ ውጤታማ ሰው ተኮር ስራዎች መስራቱ እና አሁንም እየሰራ…

Read More