Trendings

የክልሉ የድጋፍና ክትትል ቡድን በካፋ ዞን ወቅታዊ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎችን ስያካሂድ የነበረውን አፈጻጸም እየገመገመ ይገኛል።

ግምገማው በዋናነት በመደበኛ በፓርቲ ስራዎችና በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ የተቀመጡ ሀገራዊ 6ቱ የትኩረት አቅጣጫ ግቦችን ስኬታማ ለማድረግ በዞኑ እየተሰራ ያለው አፈጻጸም በጥንካሬና በጉድለት በመገምገም ተግባራቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ ሰሌዳ ስኬታማ ለማድረግ ታሳብ ያደረገ ነው። ለግምገማ መድረኩ የተዘጋጀውን የዞኑን ወቅታዊ አፈጻጸም ሪፖርት የካፋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ታከለ ታምሩ እያቀረቡ ይገኛል…

Read More

አርሶና አርብቶ አደሮችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ የመሬት አጠቃቀም ሥርዓት እንዲቀየርና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲሻሻል በልዩ ትኩረት መሥራት ያስፈልጋል ፦አቶ ፍቅሬ አማን

የገጠር መሬት ባለይዞታዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ላይ ትኩረት ያደረገ የንቅናቄ መድረክ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። መድረኩ ”ዲጂታል ማንነት ለተረጋገጠ የይዞታ ባለቤትነትና ለላቀ የፋይናንስ ተጠቃሚነት’ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን ይህም የክልሉ ግብርና ቢሮ ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር በጋራ ትብብር ያዘጋጀው ነዉ። በመድረኩ የክልሉ መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለጹት፣…

Read More

ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት የላትም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ለቀይ ባህር ስትል ኤርትራን የመውረር ፍላጎት እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ፍላጎት እንነጋገር፣ ሰጥቶ በመቀበል መርህ፣ ህዝቦች በሚጠቀሙበት መርህ እንወያይ የሚል ነው ብለዋል። የኤርትራ ህዝብ የሚያስፈልገው ልማት ነው፣ ተባብረን መልማትና መስራት እንጂ አንዱ አንዱን መውጋት የእኛ እቅድ አይደለም ነው ያሉት፡፡ ኢትዮጵያ ላይ ማንም ሀገር ወረራ ሊፈጽም እና ከጀመርነው ህልም ሊያስቆመን ይችላል…

Read More

ሪፖርታዥ

ግብርና ምርምር ለግብርናው ዘርፍ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ዘርፈ-ብዙ ነዉ። የግብርና ምርትና ምርታማነት ማነቆ መፍታት የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ፣ውጤታማነታቸው የተረጋገጡትን በማባዛትና በማላመድ ረገድ አይነተኛ ሚና ይጫወታል። በዚህም የአከባቢን ሥነምህዳር ያገናዘቡ እምቅ አቅሞችን በመለየት ለግብርና ፖሊሲ አጋዥ ሊሆኑ የሚችሉ መሠረታዊ ዳሳሳ ጥናት ማድረግና ለግብርና ተቋም ገንቢ ምክረ ሀሳብ የማቅረብ ሥራዎችንም ይሰራል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት…

Read More

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለክልሎች የሚከፋፈለው የጋራ ገቢ የድጎማ በጀት እያደገ መጥቷል፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ለክልሎች የሚከፋፈለው የጋራ ገቢ የድጎማ በጀት እያደገ መምጣቱን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። በውስን ዓላማ የድጎማ በጀቶች ትልልፍ እና በጋራ ገቢዎች ክፍፍል በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ላይ የዳሰሳ ጥናት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የሀብት ክፍፍል ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን የምክር ቤቱ አፈ ጉብኤ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል። ከዚህ ውስጥ…

Read More

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ-ርዕይ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሥራዎችን ሰንዶ ማስቀመጥ የተቻለበት ነው-አምባሳደር ብርቱካን አያኖ::

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ-ርዕይ ለቀጣይ የዲፕሎማሲ ሥራ ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ ሥራዎችን ሰንዶ ማስቀመጥ የተቻለበት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ገለጹ። አውደ-ርዕዩ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ብሔራዊ ጥቅሟን አስከብራ ለመዝለቅ ያደረገችውን ጉዞ እና ዲፕሎማሲያዊ ከፍታዋን ያሳየ መሆኑንም ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ፤ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ-ርዕይን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።…

Read More

ኢትዮጵያ በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ባስመዘገቡት አኩሪ ውጤት ኮርታባቸዋለች::

በ13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስፖርተኞች ፈታኙን ሞቃታማ የአየር ንብረት በመቋቋም ባስመዘገቡት አመርቂ ውጤት ኢትዮጵያ ኮርታባቸዋለች ሲሉ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ ገለጹ። በጋና በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ስምንተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል። ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳን ጨምሮ በሚኒስቴሩ የስፖርት…

Read More

ፌስቡክ በመጠቀም የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ የእስራት እና የገንዘብ ውሳኔ መቀጣቱን በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

ፌስቡክ በመጠቀም የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃ ሲያሰራጭ የነበረው ግለሰብ የእስራት እና የገንዘብ ውሳኔ መቀጣቱን በዳውሮ ዞን የታርጫ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡ ተከሳሽ አስራት ወልዴ (ዶ/ር) የእስራት ቅጣቱ ሊወሰንበት የቻለው ማኪራ ኮፊ፤ካፋ ቲየብ(kafa Tube እና Asrat Wolde በሚሉ ፌስቡክ አካውንት በመጠቀም የጥላቻ እና ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ጥፋተኝነቱ በማስረጃ በመረጋገጡ ነው፡፡ ተከሳሽ አስራት ወልዴ (ዶ/ር)…

Read More

በአገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን ባለው ሂደት 12 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመኸር ሰብል ተሸፍኗል-ዶክተር ግርማ አመንቴ

በአገር አቀፍ ደረጃ እስካሁን ባለው ሂደት 12 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በመኸር ሰብል መሸፈኑን የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ ገለፁ። 2016 በጀት ዓመት ከግብርና ግብዓት ስርጭት ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ ችግሮችን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ለመቅረፍ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ የግብርና ሚኒስቴር የ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እና የ2016 ዓ.ም በጀት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ በመድረኩ የእርሻና ሆልቲካልቸር፣ የእንስሳት…

Read More