“ሀላላ ኬላ” – 350 ዓመታትን የፈጀው ታሪካዊው የድንጋይ ካብ
የሀላላ ድንጋይ ካብ (ሀላላ ኬላ) የዳውሮ አባቶች በአገር በቀል ዕውቀት ድንጋይን በድንጋይ ላይ በማነባበር የገነቡት ግዙፍ እና ረዥም የድንጋይ ግንብ ነው። የሀላላ ካብ በ1 ሺህ 532 ዓ.ም በዳውሮ የመጀመሪያ ንጉሥ ስራው ተጀምሮ እስከ 18ኛው ክፍለ ዘመን ዳውሮን ያስተዳድሩ በነበሩ 14 ነገሥታት በቅብብሎሽ የተገነባ እንደሆነ ይነገራል። አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ 350 ዓመታት የወሰደ ሲሆን በንጉሥ ካዎ ሀላላ…
