የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ በታርጫ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ጤናማ ዜጋን ለመፍጠር ኢንስቲትዩቱ በክልሉ የጤና ስጋት የሆኑ በሽታዎችን የመለየት፣ ቅድመ ዝግጅት የማድረግ፣ ለህብረተሰቡ ግንዛቤ የመስጠትና የመከላከል ስራ እየሰራ ያለው አንጋፋ ተቋም መሆኑን አብራርተዋል። የመረጃ ጥራት ለማሻሻልና ከዚህ በመነሳት አስፈላጊውን የግብዓት ችግርን ለማቅረብ፤ መረጃውን ዲጂታላይዝ በማድረግ የመረጃ ጥራትን ለማሻሻል በትኩረት እየተሰራ…
