ለሸክ ኖኖ ቋንቋ ዘላቂ ዕድገትና ጥበቃ ማድረግ የአካባቢውን ባህልና የማንነት መሠረት ከመጠበቅ አንፃር ወሳኝ ጉዳይ ነው፦አቶ አልማው ዘውዴ
የሸካቾ ብሔረሰብ የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም በሸካቾ ባህል፣ቋንቋና ሀገር በቀል ዕውቀት ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶበት ተጠናቋል። የሸክ ኖኖ ቋንቋን ዘላቂ ዕድገትና ጥበቃ የማረጋገጡ ተግባር የሁሉንም አካላት የተቀናጀ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑ ተመላክቷል። የሀገር በቀል ዕውቀት የአንድ ማኅበረሰብ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ መሠረት በመሆኑ ዕውቀቱን መጠበቅና ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም ተገልጿል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል…
