ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም ጉቦ የተቀበለ አመራርን ለህግ ማቅረቡን የክልሉ ስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ገለጸ።
ህብረተሰቡ አገልግሎትን በምልጃና ጉቦ ለመፈፀም የሚፈልጉ አመራርና ሰራተኞች ላይ የተለመደውን ጥቆማ በመስጠት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ኮሚሽኑ ጠይቋል። የክልሉ የስነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነርና የሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ኮሚሽነር ዳግም ዳንኤል እንደተናገሩት ኮሚሽኑ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከህብረተሰቡ የሚደርሱ ጥቆማዎችን መሰረት በማድረግ የማጣራትና በህግ ስልጣን ለተሰጣቸው የፍትህ አካላት እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል። ኮሚሽነር ዳግም…
