የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የገጠርና ከተማ ዕድገት ማመጣጠን እንደሚገባ ተጠቆመ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ በልዩ ልዩ የኢንዱስትሪ ስትራቴጅዎችና ፖሊሲዎች ፤በገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽን እና ዲጂታላይዜሽን ላይ ለካፋ ዞን የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በቦንጋ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል። የገጠር ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ የገጠርና ከተማ ዕድገት ማመጣጠን እንደሚገባ የገለጹት የቢሮው ኃላፊ አቶ ግዛው ጋጊያብ ስልጠናው የዘርፉ ባለሙያዎችና አመራሮች የመንግሥት ዓላማና ተልዕኮ ለመፈጸም ግንዛቤ የሚያሳድግ እንደሆነ ተናግረዋል።…
የፓርቲው የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎችን ማጠናከር ይገባዋል
የስነ-ምግባር መከታተያ ክፍሎች ተልዕኮአቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ድጋፉን እንዲያጠናከር የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አመለከተ። የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በየደረጃው ከሚገኙ የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን አባላትና አመራሮች ጋር በፀረ ሙስና ትግልና ስነ-ምግባር ግንባታ ላይ በትብብር መስራት በሚቻልበት ሂደት ላይ መክረዋል። የፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)…
ነገ በክልላችን የሚጀመረዉ የተቀናጀ የተፋስሰ ልማት ሥራ ህብረሰቡ በንቃት አንዲሳተፍ አቶ ማስረሻ በላቸዉ ጥሪ አቀረቡ
የ2017 የማህበረሰብ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በክልላችን “የአፈር ሀብታችን ለብልጽግናችን”በሚል መሪ ቃል በጥር 22/2017 ዓ.ም ይጀመራል ያሉት የክልላችን ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉ የተፈጥሮ ሀብት መመናመን እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል። የዘንድሮው 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የማህበረሰብ ተፋሰስ ልማት የተፈጥሮ ሀብት የመሬት ፣ የውሃና የሰው ሀብታችንን መጠበቅ ፣ ማልማትና…
የክልሉን ሕዝቦች የጤና ደህንነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስመዝገባቸውን ቢሮው አስታወቀ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት፣ የወባ በሽታ ጫና መቀነስና የጤና መድህን ተደራሽነትን በማረጋገጥ ረገድ ስኬታማ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ። የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለጹት፤ በክልሉ የእናቶችንና የሕፃናትን ጤና ለመጠበቅ በተደረገው ጥረት የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት ከፍተኛ ውጤት…
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የወጣቶች ምክር ቤት ተመሰረተ::
ዛሬ በተደረገዉ ምክር ቤት ምስረታ 13 ሥራ አስፈጻሚና 42 የምክር ቤት አባላት ተመርጠዋል። ምክር ቤቱ ወጣት ይስሃቅ ንጉሴን የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ና ወጣት ትህትና ቆጭቶን ምክትል ሰብሳቢ በማድረግ መርጠዋል። በክልሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ፡ ገናና የሆነ ሀገር የትክክለኛ ትርክት ውጤት ስለሆነ ብሔራዊነት ገዥ ትርክታችን ሆኖ እንዲገነባ…
የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል። ቀይ ባህርን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና…
ድል የቀናው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የታዳጊዎች እግር ኳስ ውድድር በአዳማ
ስፖርታዊ ውድድር በዜጎች መካከል ማህበራዊ ትስስርና አንድነት በማጠናከር ለማህበራዊና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሚናው የጎላ መሆኑን የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በኦሮሚያ ክልል አስተናጋጅነት ሀገር አቀፍ የታዳጊ ወጣቶች ስፖርት ስልጠና ምዘና ውድድር “የታዳጊ ስፖርተኞች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ”በሚል መሪ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ውድድሩ እንደአገር በ15 የስፖርት አይነቶች እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን…
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሻግዳን ኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን ፕሮጀክት ጉበኙ
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሻግዳን ኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን ፕሮጀክት ጉበኙ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በኦሞ ቁጥር-3 ስኳር ፋብሪካ አካባቢ የሚገነባውን የሻግዳን ኤሌክትሪክ ሰብስቴሽን ፕሮጀክት ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ጉብኝት አድርገዋል። የኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የተከበሩ አቶ እሸቱ ገ/ማርያም የምርጫ ክልላቸው የሆነውን የማጂ ወረዳ እና አካባቢውን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለውን የሻግዳን የኤሌክትሪክ ሳብስቴሽን…
የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጠናከር የብልጽግና ፓርቲ ጉዞን እውን ለማድረግ አመራሩ እና አባሉ በቁርጠኝነት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለፀ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የቴፒ ብዝሃ ማዕከል የክልል ሴክተር የብልጽግና ፓርቲ ህብረት የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ በቴፒ ከተማ አካሂዷል። በአባላት ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት ቴፒ ብዝሃ ማዕከል የብልጽግና ፓርቲ ህብረት ሰብሳቢ አቶ ደምሴ ደንቦ የፓርቲውን አሰራሮች እና አደረጃጀቶችን በማጠናከር የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጉላት ተግባራትን የመምራት…
