Trendings

የሸካ ዞን የብልፅግና ፓርቲ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቴፒ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ ከፓርቲው እሳቤና መርሆዎች ተነስቶ ተቋማት የተጣለባቸውን የህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአመራር መሪነት የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር የሚገመግም መሆኑ ተገልጿል። የግምገማ መድረኩን እየመሩ የሚገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ እንደገለጹት የመድረኩ ዋና ዓላማ የፓርቲውን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል እና የታዩ ክፍተቶችን በግልጽ በመወያየት የአመራሩን የመፈጸም አቅም ማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል። የአመራር…

Read More

የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመረ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን በምክር ቤቱ የጉባኤ አዳራሽ ለእለቱ የተያዙ አጀንዳዎችን በማጽደቅ ውይይቱን ማካሄድ ጀመሯል፡፡ ምክር ቤቱ ስድስተኛ የፓርላማ ዘመን፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ቃለጉባዔውን መርምሮ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ የቀጠለ ሲሆን በጉባኤው ያጸደቃቸውን ሌሎች አጀንዳዎች በዝርዝር ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍባቸው ይጠበቃል።

Read More

ሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ስራዎች የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል በትኩረት ይሰራል፦ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

በሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ስራዎች የተገኙ ውጤቶችን ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የብሄራዊ ደህንነት ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ቀንአ ያደታ (ዶ/ር) የተመራ የክትትልና ድጋፍ ቡድን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አጠቃላይ የኮሙኒኬሽን ስራዎች ዙሪያ ዛሬ ምልከታ አድርጓል። ቡድኑ ከአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም ተወያይቷል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር…

Read More

ሰላምን በተመለከተ

መንግስት ለትችት ክፍት ነው። በሚያነሳው ሃሳብ ምክንያት የታሰረ አንድም ሰው የለም። ነገር ግን በአንድ እጅ ሰላማዊ ትግል፤ በሌላ እጅ በጦርነት መንግስት ለመጣል የሚሞክሩ ኃይሎች አሉ። ይህ ህግን መጣስ ነው። ነጻነትን በአግባቡ የማስተዳደር ችግር አለ። ነገር ግን መንግስት አሁንም ለሰላም ጽኑ አቋም አለው። ችግሮች በድርድር እንዲፈቱ ነው የምንሻው። ባለፉት 7 ዓመታት ከየትኛውም የጎረቤት ሀገራት ጋር ጦርነት…

Read More

የምግብ ስርዓት ለውጥ ፍኖተ ካርታና ክላስተር 7 ማስተዋወቂያ ስልጠና በቦንጋ ከተማ ተጀመረ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የምግብ ሰርዓትና የስርዓተ–ምግብ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ዩኒት ከአግሪካልቸራል ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI) ጋር በመተባበር በ“የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን የፍኖተ ካርታ ወርክሾፕ እና ክላስተር 7 ግንዛቤ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ፕሮግራም በቦንጋ ከተማ እየሰጠ ይገኛል። ስልጠናው በክልሉ የምግብ ስርዓትን በዘላቂነት፣ በተቀናጀ አቀራረብ እና በክላስተሪንግ ስርዓት ለመለወጥ የሚያግዙ ዋና ዋና አቅጣጫዎች ላይ…

Read More

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ሁሉም ዜጋ የሚጠበቅበትን ሊወጣ ይገባል ተባለ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብዝሃ ከተማ በሆነችዉ ቴፒ ከተማ ለሚገኙ የክልል ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አስመልክቶ ስልጠና መስጠት ተጀምሯል። ስልጠናዉ በዋናነት ሀገሪቲ ያላት ስትራቴጂካዊ ብሔራዊ ጥቅሞች ምንድናቸዉ ፣ ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ያሉ ዕድሎችና ፈተናዎች ምን ድናቸዉ እንዲሁም የመፍትሔ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል። የሀገራችን ሲቪል ሰርቫንቱና እያንዳንዱ ዜጋ መወጣት ስላለበት ኃላፊነትና ከተለያዩ…

Read More

ባለፉት 3 አመታት ህብረተሰቡ በማስተባበር የተለያዩ የመንገድ ልማት ስራዎች ተሰርተዋል።አቶ ፋጂዮ ሳፒ

በክልሉ በ3 ዓመታት ዉስጥ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎና ከአጋር አካላት በተገኘ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ከ1ሺ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ መስራት መቻሉን አቶ ፋጂዮ ሳፒ ተናገሩ። የ122 ኪሎ ሜትር የአዲስ መንገድ እና ጥገና ስራ በቅርቡ እንደሚጀመርም ኃላፊው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቁመዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና…

Read More

የጉባ ብስራቶችና የመደመር መንግስት ትሩፋቶች ላይ በህዝብና በመንግስት ቅንጅት የመጣው ለውጥ የሀገራችን ከፍታ ያሳየ ነው ተባለ

በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተማ አቀፍ የህዝብ ውይይት መድረክ መካሄድ ጀምረዋል። በመድረኩ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የማሻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አንዷለም ጌታቸው የጋራ ልማትና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ቀጣይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ‎‎‎‎‎‎‎በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ…

Read More

በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሁለንተናዊ ስርዓተ ምግብ ለመፍጠር እየተሰራ ነው – ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)

በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ሁለንተናዊ ስርዓተ ምግብ ለመፍጠር በጋራ እየተሰራ ነው ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ስርዓተ-ምግብ የአየር ንብረት ለውጥ ሊያደርስ ለሚችለው ተፅዕኖ ምላሽ መስጠት ላይ ትኩረቱን ያደረገ መድረክ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)÷ ለዓለም ስጋት እየሆነ የመጣው የአየር ንብረት ለውጥ በተለይ በዜጎች የአመጋገብ ስርዓት ላይ የከፋ ተፅዕኖ እንዳያደርስ ኢትዮጵያ…

Read More