የህብረተሰቡን የሰላምና የልማት ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ዙሪያ የመከረው ፎረም ቀጣይ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።
በፎረሙ ላይ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መሀመድ እድሪስ ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሁለቱ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ተጋባዥ አካላት ተገኝተዋል። በመድረኩ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን በመስጠት በህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በመቅረፍ ለዘላቂ ሰላምና ልማት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ። በአንድ አካባቢ በህብረተሰቦች መካከል የሚፈጠረው ግጭት እየተባባሰ ሌላ የከፋ አደጋ እንዳያስከትል አመራሩ በሰከነ መንገድ…
