Trendings

ጠቅላይ ሚኒስር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ስለባሕር ዳር ልምድ ያነሷቸው ነጥቦች

ዛሬ የባሕርዳርን ከተማ የኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ ተመልክቻለሁ። ተፈጥሮ እና የሰው ጥበብ ተዋሕደው ባሕርዳርን ይበልጥ ውበቷን እያወጡት ነው። ከተማዋን የንግድና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ አመራሩ ከሚያደርገው ጥረት የምንማራቸው ብዙ ነገሮች አሉ። 1. ባሕር ዳር በፈተና ውስጥ የመጽናት ምሳሌ ናት፤ ባለፉት ዓመታት የነበረው ፈተና እያለፈ ነው። ባሕር ዳር በፈተናው ውስጥ ሥራዋን አላቋረጠችም። እንዲያውም ለፈተና የተወረወረውን ድንጋይ ለግንባታ ተጠቅማበታለች።…

Read More

የጤና መድኅንን ለማስቀጠል የፋይናንስ ዘላቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ተባለ

የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ፣ ፍትህ ቢሮ፣ ከፋይናንስ ቢሮ እና ከዋና ኦዲት ቢሮ ከተውጣጡ ኃላፊዎች እና ጥሪ ከተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር፣ የጤና መድኅንን ለማስቀጠል እና የፋይናንስ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ በሚተገበሩ ተግባራት ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ የጤና መድኅን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፣ የማህበረሰብ ዓቀፍ ጤና መድኅን ለማስቀጠል የፋይናንስ…

Read More

ፓርቲያችን ብልፅግና ትላንት የሥርዓተ መንግስት አስተዳደራችን አንድ አካል ሆነው ካለፉ ልንቀይራቸው ከማንችላቸው ታሪኮች ጋር ፈፅሞ ፀብ የለውም፡- አቶ አደም ፋራህ

ፓርቲያችን ብልፅግና ትላንት የሥርዓተ መንግስት አስተዳደራችን አንድ አካል ሆነው ካለፉ ልንቀይራቸው ከማንችላቸው ታሪኮች ጋር ፈፅሞ ፀብ የለውም ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ። ፓርቲው በመርህ ደረጃ ከትላንት ተምሮ፣ ዛሬን አሳምሮ፣ ነገን የተሻለ ማድረግን በማመን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በመትጋት ላይ እንደሚገኝ በማሕበራዊ ትስስር…

Read More

53ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 53ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ 1. በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው መደመር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው በአዋጅ ቁጥር 1294/2015 መሠረት ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ የሚቋቋም ሲሆን በዘርፉ ወጣቶችን ለማሰልጠንና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ የሆኑ ምሁራንን ለማፍራት የሚሰራ ነው፡፡ ደንቡ የዩኒቨርሲቲውን ተግባርና ሃላፊነት…

Read More

ክልላዊ የአርሶ አደር የመስክ ላይ ትምህርት ቤት ተቋማዊ ማድረጊያ ፕሮግራም በጊምቦ ወረዳ ተካሄደ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአርሶ አደር የመስክ ላይ ትምህርት ቤት (FFS Institutionalisation) ተቋማዊ ማድረግያ ፕሮግራም በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ሃማኒ ቀበሌ ተካሂዷል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የካፋ ዞን ግብርና ደን፣ አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አክሊሉ አማዴ የኤስ ኤን ቪ ፕሮጀክት ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በዞኑ በ6 ቀበሌዎች በአትክልትና ፍራፍሬ ወጣቶችና ሴቶችን በማደራጀት…

Read More

የምዕራብ ኦሞ ዞን ውብ ምድር

የምዕራብ ኦሞ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ዞኖች አንዱ ነው። ዞኑ የሜኤን፣የዲዚ፣የሱሪና ዚልማም ብሔረሰቦች እና ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አብረው ተዋደው፣ተጋብተው፣ተዋልደው፣ሀብት አፍርተው በፍቅር የሚኖሩበት አካባቢ ነው። የምዕራብ ኦሞ ዞን በሰብል አብቃይነቱ ፣ በወርቅና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት ከመገለጫዎቹ ዋናዎቹ ናቸው። ዞኑ በርካታ የውጭ ሀገራትን ቀልብ የሚስቡ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህቦች የሚገኙበት ዞንም ነው። በዚሁ ምዕራብ…

Read More

መንግሥቴ የሚመሰገን ከሆነ በዕዳ አያያዝ በሠራው ሥራ መሆን አለበት፡-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን የዕዳ ጫና በመቀነስ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን ገለጹ። ኢትዮጵያ ከለውጡ በፊት በከባድ የዕዳ ጫና ውስጥ እንደነበረች ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በተለይም ቀደም ሲል ይወሰድ የነበረው የንግድ ብድር ለሀገሪቱ ትልቅ ፈተና እንደነበር ጠቁመዋል። ይህ ዓይነቱ ብድር የሀገሪቱን የፋይናንስ አቅም በማዳከሙ፣ አበዳሪዎች ተጨማሪ ብድር ለመስጠት ተጠራጥረው እንደነበርም አብራርተዋል። የሌብነት መስፋፋት እና…

Read More

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የሚቀመጡ ተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ ነው::

በ2016 ዓ.ም በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ የሚቀመጡ ተማሪዎች ምዝገባ ከየካቲት 3 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል። አገልግሎቱ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የምዝገባ ሂደትን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ዘንድሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ መልቀቂያ ፈተና ማከናወን የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ መሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ…

Read More

የዘንድሮ “ማሽቃሬ ባሮ” በድርርብ ስኬቶች እና ደስታዎች የታጀበ ነው:- አቶ እንዳሻው ከበደ

የ2018 ዓ.ም የካፈቾ ዘመን መለወጫ ማሽቃሮ በዓልን አስመልክቶ የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻ ከበደ መግለጫ ሰጥተዋል። በዓሉ ለዓመታት መከበር ካቆመ በኃላ በ1986 ዓ.ም የባህል እና ቋንቋ ስምፖዚዬም መካሄዱን ተከትሎ በ1998 ዓ.ም በድጋሜ መከበር መጀመሩን ያወሱት ዋና አስተዳዳሪው ዘንድሮ በልዩ ድምቀት ድምቀት ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል። በዓሉ ህዝባዊ መሠረት ያለው በመሆኑ ላለፉት 20 ዓመታት ወቅቱ…

Read More