የፕሮግራም በጀት አሰራር ስርዓቱን በየተቋማት ተግባራዊ በማድረግ ስራዎችን በውጤት ለመለካት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲቻል በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፋይናንስ ቢሮ በፕሮግራም በጀት አሰራርና አተገባበር ዙሪያ በክልሉ በሚገኙ ለዘርፉ አመራሮች የተዘጋጀዉ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየተሰጠ ይገኛል። የስልጠናው ዓላማ የፕሮግራም በጀት አሰራርና አተገባበር፣ ክትትልና ሪፖርትን ለመለካት የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓት ላይ የተሻለ ግንዛቤ ለመፍጠር ነው ተብሏል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ከዚህ በፊት የነበሩ…
