Trendings

የሲንጋፖር ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

የሲንጋፖር ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድል በመጠቀም በኢትዮጵያ በግብርና እና ሌሎች ዘርፎች ኢንቨስት እንዲያደርጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ጥሪ አቀረቡ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሲንጋፖር ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሲንጋፖር አቻቸው ቪቪያን ብላከሪሽናን (ዶ/ር) ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው እንዲሁም የጋራ ትብብርን…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ሚዲያ ኔትወርክ በድህረገጽና በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍ የሥራ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር በታርጫ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ከሚዲያ ኔትወርኩ ዘርፎች አንዱ የኾነው የድህረገጽና ማህበራዊ ሚዲያ ይፋዊ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ የሚዲያ ኔትወርክ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ እና የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍቅሬ አማንን ጨምሮ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል። የክልሉ መንግሥት ከምሥረታው ጀምሮ በርካታ የልማትና መልካም አስተዳደር ግንባታ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑንና በዚህም አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ…

Read More

ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን የሚለው ራዕይ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ስለመሆኑ ውጤቶቻችን ማሳያ ናቸው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ

ኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን የሚለው ራዕይ በትክክለኛ አቅጣጫ ላይ ስለመሆኑ ውጤቶቻችን ማሳያ ናቸው- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናታለም መለሰ እንደ ሀገር ጥራት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትንና የጋራ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስራዎችን እንዲሁም አካታችና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያረጋግጥ የብዝሃ ዘርፍ የልማት ስትራቴጂ በመከተል እየሰራናቸው ያሉ ስራዎች በሁሉም መስኮች ፍሬ እያፈሩና የኢትዮጵያን በ2023 አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት እናደርጋለን በሚል…

Read More

ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ማሳካት በሚያስችል መልኩ ዝግጅት እየተደረገ ነው

በ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ማሳካት በሚያስችል መልኩ ውጤታማ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአረንጓዴ አሻራ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ(ዶ/ር) ገለጹ። አስተባባሪው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ዘንድሮ የሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር፣ የመጀመርያው ምዕራፍ ማጠቃለያ ዓመት በመሆኑ ዝግጅቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡ በዚህም በዘንድሮው መርሃ-ግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ7 ነጥብ 5…

Read More

በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ

በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ እየታደሙ የሚገኙ የጎረቤት ሀገራት እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች እንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል። ብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን ” ከቃል እስከ ባህል ” በሚል መሪ ሀሳብ ከትላንት ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል። በጉባኤ ላይ ለመታደም ከተለያዩ ጎረቤት ሀገራት የመጡ እህት ፓርቲዎች እና የብሪክስ አባል ሀገራት እህት ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች…

Read More

ባህልን አልምቶ ተንከባክቦ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባ የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ገለጹ።

የቤንች ብሔር ዘመን መለወጫ “ቢስት ባር ” በፓናል ውይይት በሲዝ ከተማ እየተከበረ ነው። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን ቢስት ባር የህዝቦችን የእርስ በርስ ትስስር የሚያጠናክር በዓል ነው ሲሉ ተናግረዋል ። ቢስት ባርን የበለጠ እንዲለማም ከቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር አብሮ በማስተሳሰር ማሳደግም ይገባል ብለዋል። ቢስት ባር ካለው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች የተነሳ ትልቅ የሀገር ሀብት…

Read More

የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ዘርፍን ለማጠናከር ያለመ ዉይይት በዳዉሮ ዞን ተካሄደ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በዳዉሮ ዞን የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ሥራዎችን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ የውይይት መድረክ በዳውሮ ዞን ተካሂዷል። በክልሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ በአቶ የሺዋስ ዓለሙ የተመራ የአመራር ቡድን ከዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በየደረጃው የሚገኙ የኮሙኒኬሽን መዋቅሮችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ምክክር አድርጓል። የሚዲያ ሚና ለልማት ስኬት ወሳኝ ነው አቶ…

Read More

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 38ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ በዚህም መሠረት፦ 1ኛ.የ37ኛ መደበኛ ጉባዔ ቃለ ጉባዔን አፅድቋል። 2ኛ.በመቀጠልም የቀረቡ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ጥያቄዎች ላይ ተወያይቷል። በዚህም የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን 9 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን መርምሮ በግብርና፣በእንዱስትሪና አገልግሎት የስራ ዘርፎች ለመሰማራት 527 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል መጠን…

Read More

የማሽቃሮን ዕሴት በማዳበር ለልማትና ለህብረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ ማዋል ይገባል – ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ (ማሽቃሮ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች፣ የባህል መሪዎች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የነገስታት መናገሻ በኾነውና ከቦንጋ ከተማ አቅራቢያ በሚገኘው “ቦንጌ ሻምበቶ” ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የማሽቃሮ ዕሴት የኾኑ አብሮነትና አንድነትን በማጠናከር ለልማትና ለኅብረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ ማዋል…

Read More

በክልሉ 9 ወራት 77 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ተደርጓል፦ አቶ ግዛው ጋግያብ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ የ9 ወራት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ አድርጓል ። ባለፉት 9 ወራቶች ከፈጻሚ ዝግጅት ጀምሮ በቢሮው የተሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመወጣት እንዲያስችል ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን የቢሮ ኃላፊው አቶ ግዛው ጋግያብ ተናግረዋል ። ቢሮው በአይሲቲ እና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች በተጠናቀቀው 9 ወራቶች በዋና ዋና ተግባራት የተሻሉ ስራዎች መከናወናቸውንም ገልጸዋል ።…

Read More