የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅት ላይ በነበረችበት ጊዜ ከጎኗ በመቆም እውነተኛ አጋርነቷን ያስመሰከረች ሀገር ናት – ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሼህ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ኢትዮጵያ ፈታኝ ወቅት ላይ በነበረችበት ጊዜ ከጎኗ በመቆም እውነተኛ አጋርነቷን ያስመሰከረች ሀገር እንደሆነች ዶ/ር ጌዲዮን ገልጸዋል። የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት እና የሕዝቦቹን ወንድማማችነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሠሩም…
