የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን የካቲት 5 እና 6 እንደሚያካሄድ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ገልፀዋል።
የ2018 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የአስፈፃሚ አካላት ስራ ሪፖርትን ጨምሮ ሌሎች አጀንዳዎች በጉባኤው እንደሚቀርቡም አመላክተዋል። ከጉባኤው አስቀድሞ ምክር ቤቱ በቋሚ ኮሚቴና በጽ/ቤት አማካኝነት በግማሽ ዓመት ለማከናወን ካቀዳቸው ተግባራት መካከል በተለይም የድጋፍና ክትትል እንዲሁም የቁጥጥር ስራዎችን በ5ቱም ዘርፍ ሰርቶ ማጠናቀቁን የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አሳውቀዋል። በተጨማሪ የቋሚ ኮሚቴ ስራ ሪፖርት ተገምግሞ ግብረ መልስ ተሰጥቷል ብለዋል። ከግምገማው በኋላ እንደ ክልል…
