Trendings

Getenesh Gebeyehu

የሚዛን አማን ከተማ የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር፣ ከተማዋን በቴክኖሎጂ በማዘመን ለነዋሪዎቿ ምቹና ተመራጭ ለማድረግ ያለመውን የ’ስማርት ሲቲ’ ፕሮጀክት በተጨባጭ እርምጃ ጀመረ። ይህ ታላቅ ራዕይ እውን እንዲሆን የሚያስችለው የጥናትና ቅየሳ ሥራ፣ በከተማው ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊ እና በሌሎች ከፍተኛ አመራሮች አማካኝነት በሚዛን ጋቸብ ሰከንደሪ ሳይት በይፋ ተጀምሯል። የከተማ አስተዳደሩ ከ”ምን ያምር ከተማ ፕላንና ተያያዥ ሥራዎች” አማካሪ ድርጅት ጋር በገባው…

Read More

አጦ መንትያ ተራራ፡ የዳውሮው ግርማ ሞገስና የሃላላ ኬላው ዘብ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ የዳውሮ ዞን ልብ ውስጥ፣ አንድ ግርማ ሞገስ የተላበሰ ተራራ የንጉሥ ሃላላ ኬላን ታሪካዊ ስፍራ ከፍ ብሎ በትኩረት የሚጠብቅ ይመስላል። ይህ በሎማ ቦሣ ወረዳ የሚገኘውና የአካባቢው ድምቀት የሆነው ተራራ አጦ መንትያ ይሰኛል። ከባህር ጠለል በላይ በ3 ሺህ ሜትር ከፍታው የሰማይ ጉልላትን የሚዳስስ የሚመስለው ይህ ተራራ፣ ከ17 ሺህ ሄክታር በላይ በሆነው ሰፊ ግዛቱ አስደናቂ…

Read More

ለበሽታ መከላከልም ሆነ የህክምና አገልግሎት ውጤታማነት ተግባቦት ወሳኝ በመሆኑ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ኃላፊነታቸውን በተገቢው መወጣት አለባቸው፦ አቶ ኢብራሂም ተማም

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የጤና ቢሮ 4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እና የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመከታተልና ለመቆጣጠር ከኃይማኖት አባቶች፣ ከሚዲያና ከህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ጋር የምክክር መድረክ በታርጫ ከተማ አካሂደዋል። የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃፊው አቶ ኢብራሂም ተማም የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በክልሉ ሁሉም አካባቢ እስከ ቀበሌ ድረስ እንደሚሰጥ ተናግረዋል። 4ኛ…

Read More

የክልሉን የማዕድን ሀብት በተገቢው በማልማት ለክልሉ ልማት ማዋል ይገባል – አቶ ፍቅሬ አማን

የደቡብ ምዕራብ ማዕድን ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፥ ኮርፖሬሽኑን በይፋ ሥራ ማስጀመር በሚቻልበት አግባብ ላይ በቦንጋ ከተማ መክሯል። በውይይቱ ላይ የቦርድ ሰብሳቢ፥ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፥ ክልሉ በተፈጥሮ ሀብት የታደለ በርካታ የገፀ ምድርና ከርሰ ምድር የማዕድ ሀብት ያለበት መኾኑን በመጠቆም፥ ይህንን የማዕድን ሀብት በተገቢው በማልማት ለክልሉ ልማት ማዋል ይገባል ብለዋል። ተግባራዊ በኾነው…

Read More

“መሠረታዊ ችግሮችን በድፍረት መፍታት”

‎የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ መዋቅራዊና አሁናዊ ችግሮች ነበሩበት። በዕዳ ጫና የጎበጠ፤ የውጭ ምንዛሬ እጥረት የገጠመውና ባልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች የተሣሠረ ነበር። ‎እንዲሁም ደግሞ የውጭ_ኢንቨስትመንትንና የውጭ ካፒታልን በሚገባ ለመቀበል ያልተዘጋጀ የኢኮኖሚ ሂደት ነበረው። ‎ይሄንን ችግር ለመፍታት የመደመር መንግሥት የተጠናና ደፋር ውሳኔ ወስኗል፡፡ ይሄም የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ነው፡፡ ‎የመደመር መንግስት መጽሐፍ ገፅ 89

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸለመ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በ2017 የበጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ጋር ባደረገው ጠንካራ ውድድር 3ኛ ደረጃን በመያዝ ታላቅ ስኬት አስመዝግቧል። ይህ እውቅና የተሰጠው፣ ጥብቅ በሆነ ሀገር አቀፍ የአቻ ለአቻ ምዘናና ግምገማ ሲሆን፣ ኮሚሽኑ ላስመዘገበው ድንቅ ውጤት የማበረታቻ ሽልማትና ሰርተፍኬት ከኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ…

Read More

የግብርናና ገጠር ልማት ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን እውን ለማድረግ የአመራርና የባለሙያ ውጤታማነት ሊጠናከር ይገባል፦ አቶ ማስረሻ በላቸው

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮና ተጠሪ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ያለፉት አምስት ወራት የተግባር አፈፃፀም ግምገማ እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በግብርናው ሴክተር የተለያዩ የንቅናቄ ሥራዎችን በመምራት ከመኸር ወጥተን ወደ በልግ መሸጋገር ወቅት ላይ መሆኑንና አዲስ…

Read More

የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በተግባር እያገዘ ይገኛል

የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በተግባር እያገዘ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት ተግባራዊ የተደረገው የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ-ግብር በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል፡፡ መርኃ-ግብሩ የአሁኑን ትውልድ ተጠቃሚነት ያረጋገጠ እንዲሁም ለመጪው ትውልድ ተስፋን የሰጠ ሲሆን በስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትናን…

Read More

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እያደረገው ያለውን ቅድመ ዝግጅት አጠናክሮ እንዲቀጥል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ። ቋሚ ኮሚቴው የቦርዱን የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እና የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት አፈጻጸምን ገምግሟል። በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለነ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ…

Read More

ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድረግ ሁለተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ

በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ሥራ ክህሎት መምሪያ የ2018በጀት አመት የ5 ወር እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ምክክር እየተደረገ ይገኛል። በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንደተናገሩት ለወጣቶች ሥራ እድል ፈጠራ የተያዙ በጀቶች በአግባቡ እና በወቅቱ ማሰራጨት እንደሚገባ አስታውቋል። ወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በማድረግ ሁለተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪ አስገንዝበዋል። ለወጣቶች በገጠር እና በከተማ…

Read More