Trendings

Getenesh Gebeyehu

በሥልጠናው የተቀመጡ ሀገራዊ የብልጽግና ግቦችን ለማሳካት የአመራር ቁርጠኝነት ፣ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ መርሆዎችን መከተል ከሁሉም ይጠበቃል፦አቶ እንዳሻው ከበደ

“በመደመር መንግሥት እይታ፤የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ሲሰጥ የቆየው የካፋ ዞን 3ኛ ዙር አመራሮች ስልጠና በስኬት ተጠናቋል ። የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ አጠቃላይ የሥልጠና ቆይታ አስመልክቶ ማጠቃለያና ቀጣይ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል:: አመራሩ የተያዙ የብልጽግና ግቦችን ለማሳካት በጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነት፣ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ዝላይ መርሆዎችን ተከትሎ በመስራት ፈጣን ለውጥ ማስመዝገብ ይጠበቅበታል ብለዋል ። ከስልጠና…

Read More

አመራሩ የልማት አቅሞችን በመጠቀምና ከህብረተሰቡ ጋር ተግባቦት በመፍጠር በቀጣይ አጭር ጊዜያት ውስጥ የሚታዩ ተጨባጭ ውጤቶች ለማስመዝገብ መስራት ይገባል፤ አቶ ታከለ ተስፉ

በኮንታ ዞን ላለፉት 9 ቀናት “በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ቃል ለ3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና እየተጠቃለለ ይገኛል። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የኮንታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ እንደ ሀገር የተጀመረው የብልጽግና ጉዞ እውን እንዲሆን በአመራሩ ዘንድ የአመለካከትና የአስተሳሰብ አንድነት መፍጠር ተቀዳሚ ተግባር ስለመሆኑ አስረድተዋል። ከዚህ መነሻ በሀገር አቀፍ…

Read More

የመንግስት ተቋማት ከመደበኛ ስራቸዉ ጎን ለጎን በሰብዓዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ፦አቶ ጥላሁን ታደመ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በታርጫ ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ አረንጓዴ መንደር ለአቅመ-ደካማ ሴት ያስገነባውን ቤት መርቀው አስረክበዋል። በርክብክቡ ወቅት የተገኙት የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጥላሁን ታደመ የመንግስት ተቋማት ከመደበኛ ስራቸዉ ጎን ለጎን በሰብዓዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ ትኩረት ሰጥተዉ እንዲሰሩ ጥሪ አቀርበዋል። አክለውም የመንግስት ተቋማት ከመደበኛ ስራቸዉ ጎን…

Read More

በክልሉ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማስፋት እና ማጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች በትኩረት እየተከናወኑ ነው

የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሰራር በመቅረፍ እንግልትን ከመቀነስ ባለፈ ጊዜና ገንዘብ በመቆጠብ ቀልጣፋ አገልግሎት የሚሰጥ በመንግሥት የተነደፈ የሪፎርም አሰራር መሆኑን የደቡብ ምዕራብ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሥራት አዳሮ ገለጹ። በሚዛን ብዝሃ ማዕከል አማን ከተማ ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የደቡብ ምዕራብ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ከጀመረ በአንድ ወር ውስጥ ከ2ሺህ…

Read More

ስልጠናው የአመለካከት አንድነትን ወደ ተግባር አንድነት ለመለወጥና ለመስራት የሚያስችል አቅም ይፈጥራል ፦ አቶ ሀብታሙ ካፍትን

በቤንች ሸኮ ዞን “በመደመር መንግስት እይታ ለዘርፎች እምርታ” የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ማጠቃለያ እየተካሄደ ይገኛል። ከህዳር 22 እስከ 30/2018 በዞን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘው የ3ኛ ዙር የመካከለኛ አመራሮች የስልጠና መድረክ ማጠቃለያ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል። የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍትን የስልጠና መድረኩን ሲያጠቃልሉ እንደተናገሩት በሀሉም ዘርፎች እየተመዘገቡ የሚገኙ ውጤቶችን ከፓርቲው እሳቤ መነሻ በማድረግ…

Read More

በክልሉ ባሉት ስድስት ዞኖች 3ተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ መመካከለኛ አመራር ሰልጣኞች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ

በመደመር መንግሥት ዕይታ፣ ”የዘርፎች እምርታ” በሚል ሃሳብ ለመካከለኛው አመራር በየማዕከሉ ላለፉት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ3ተኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራር የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰልጣኞች በየዞኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጉብኝ አደርገዋል። የጉብኝቱ ዓላማ ሰልጣኝ አመራሮች ከስልጠናዉ በተጓዳኝ በክልሉ ውስጥ በተለያዩ አካባቢ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን በመጎበኘት ልምድ ልውውጥና ተሞክሮ በመቀመር በየአካባቢው ወደ ተግባር ለመቀየር ታሳቢ ያደረገ ነው።…

Read More

የህብረት ሥራ ማህበራት የኦዲት አገልግሎት በብቃትና በጥራት ማከናወን ለማህበራት ደህንነት ጥበቃ ድርሻው የጎላ መሆኑን የክልሉ ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ለዞንና ወረዳ የህብረት ሥራ ኦዲተሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየሰጠ ይገኛል። የስልጠና መድረኩ ከካልም ፕሮግራም ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ”በህብረት ሥራ ኦዲቲንግ እና በህብረት ሥራ ኦዲት አፈጻጸም መምሪያ ቁጥር 978/2016 ዙሪያ ያተኮረ ነው። በክልሉ የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቀበሌ መንገሻ…

Read More

የኢትዮጵያ ማዕከላዊነት የሁላችን መሻት ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ በሚገኘው 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ላይ ንግግር አድርገዋል። ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የዛሬውን በዓል ያዘጋጀው እና ኢትዮጵያን ያሰባሰበውን ሀዲያን አመስግነዋል። ኢትዮጵያ አንዱ ከፍ ሌላው ዝቅ የሚልባት ሳይሆን ሁላችን የምንደምቅባት ነች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ኢትዮጵያ በሁሉም መመዘኛ ወደ ብርሃን አየተሸጋገረች ባለችበት…

Read More

የአፋር ዳጉ – ለዳውሮ ኩራቱ

የሲዳማው ጫምባላላ – ለአማራ ሀሴቱ የኦሮሞ ገዳ – ለሐረሪ ምቾቱ የአክሱም ሐውልት – ለሀዲያ ታሪኩ የጀጎል ግንብ – ለቤንሻንጉል ቅርሱ የፋሲል ቤተመንግሥት – ለሀዲያ ሀብቱ የሶማሌው ዳንቶ – ለጋሞ ባህሉ የጉራጌ ክትፎ – ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ጣዕሙ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በ20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ላይ ለመታደም በሆሳዕና ከተማ አብዬ ቦርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም ገብተዋል፡፡

20ኛው የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን “ዲሞክራሲያዊ መግባባት፤ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ እየተከበረ ነው። በብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀንን ለመታደም ከመላው ሀገሪቱ ወደ ሆሳዕና ከተማ የገቡ የበዓሉ ታዳሚዎች በአብዬ ኤርሳሞ መታሰቢያ ስታዲየም ባህላዊ ትርዕታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፡፡

Read More