የቦንጋ ቀላል የአዉሮፕላን ማረፊያ ግንባታው የተጓተተ በመኾኑ በትኩረት በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት ለማስገባት እንደሚሰራ የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን አስታወቀ

በክልሉ ነባር የአዉሮፕላን ማረፊያዎች ወደ ሥራ ለማስገባት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲሚቀጥልም ተገልጿል። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከዚህ ቀደመ አገልግሎት ይሰጡ የነባሩና በተለያዩ ምክንያቶች አገልግሎት ያቋረጡ የአውሮፕላን ማረፊያዎችን ዳግም ወደ ሥራ ለማስገባት የተጀመረው ጥረት ተጠናክረው እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሐንስ አበራ እንደገለጹት፥ በክልሉ ከዚህ ቀደመ አገልግሎት…

Read More

የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የቦንጋ መለስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አደረጉ::

የኢፌዲሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የቦንጋ መለስተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ያለበትን ደረጃ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱ የፌደራል፣የክልል፣የካፋ ዞንና የቦንጋ ከተማ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በፍቅር ከበደ

Read More

በአንድራቻ ወረዳ የጌጫ ከተማ የህዝብ መድኃኒት ቤት ተመርቆ ለአገልግሎት ብቁ ሆኗል።

የህዝብ መድኃኒት ቤቱን የክልሉ ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ መርቀዋል። በምረቃው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወሰን ጨመሰ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚቀርብበት ነው ብለዋል። በመንግሥት ተቋማት የማይገኙ መድኃኒቶች በአማራጭነት ቀርበው ህብረተሰቡ እንዲጠቀም ያግዛልም ብለዋል። ለአገልግሎት በበቃው የህዝብ መድኃኒት ቤት የሰው ሀይል ቅጥር ለማሟላት ትኩረት ተደርጎ ይሰራል ብለዋል።…

Read More

የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ለሀገር ሁለንተናዊ ለውጥ ያለውን ሚና በመረዳት ተገቢ የሆነ የኩነት መረጃን በአግባቡ መያዝና ማደራጀት እንደሚገባ ተገለፀ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የወሳኝ ኩነቶች ዘርፍ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሽፋን እና ጥራትን ለማሳደግ በሚያስችሉ ተግባራት ላይ ዉይይት ተካሂዷል፡፡ የዜጎችን መብትና ግዳታ ለማስከበር መሰረታዊ መረጃዎችን ለማደረጃት የሚስችል ተቋም ስለሆነ ለዘርፉ መሳካት በትኩረት እንደሚሰራም ተመልክቷል፡፡ በክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የጸጥታ ዘርፍ ምክትልና የወሳኝ ኩነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ደነቀ፤የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና…

Read More

የቴፒ መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያና የቡና ቅምሻ ማዕከል ተመረቅዉ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

የተመረቁት ፕሮጀክቶች የአካባቢውን ኢኮኖሚ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ፋይዳው የላቀ መሆኑም ተጠቁሟል። ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በምረቃዉ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዓመታት በቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገኘ ነው ብለዋል። በዞኑ ገበያ ተኮር የሆኑ እንደ ቡና፣ሻይና ቅመማ ቅመም ሰብሎች በስፋት የሚመረት ሲሆን የቡና ጥራት ሰርተፊኬሽን ማዕከሉ መመረቅ የተጀመረውን የብልጽግና…

Read More

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ጋር በማስተሳሰር በስፋት እየተከናወነ ነው

የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ጋር በማስተሳሰር በስፋት እየተከናወነ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሃይ ጳውሎስ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በየካ ተራራ በመገኘት ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አመራር አባላት እና ሰራተኞች ጋር የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩም ቀደም ብሎ ለአፈርና ውሃ ጥበቃ…

Read More

የቴፒ የምርት ጥራት ምርመራና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

በኢፌዲሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቴፒ የምርት ጥራትና ሰርቲፊኬሽን ማዕከል ዛሬ ተመርቋል። በምረቃው ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር)፣ የኢፌዲሪ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢፌዲሪ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአከባቢው ማኅበረሰብ ተገኝተዋል። በታጠቅ አበበ

Read More

በህብረተሰብ ተሳትፎ በቴፒ ከተማ የተገነባዉ የጎጂ ድልድይ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ድልድዩን መርቀዋል። የጎጂ ድልድይ በህዝቡ ብርቱ ትብብር የተሰራ የህዝቡ አንድነት ማሳያ ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል። ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት መልዕክት በህዝቡ ብርቱ ትብብር የተሰራ የህዝቡ አንድነት ማሳያ ፕሮጀክት ነው ሲሉ ተናግረዋል ። ህዝቡ ጉልበቱን፣ሀብቱንና ዕውቀቱን በማስተባበር የመንግስት አቅም በመሆን ላከናወኑት ተግባር በክልሉ መንግስት ስም አመስግነዋል ። ይህ…

Read More

ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና በሚዛን-ቴፒና ቦንጋ የዩኒቨርስቲዎች ፕሬዝደንቶች፣ ምክትል ፕሬዚደንቶች እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት በተገኙበት ተጀምሯል።

የሁለተኛው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተፈታኞች ፈተናቸውን በእንግሊዝኛ ትምህርት ዓይነት መጀመራቸውን ከዩኒቨርሲቲዎቹ መረጃ መወቅ ተችሏል። የሁለቱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንቶች ባስተላለፉት መልዕክት ለተማሪዎች መልካም ምኞታቸውን ገልጸው ፈተናውን ተረጋግተው መስራት እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ፈተናው ከዛሬ ጀምረው ሶስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዚህኛውም ዙር የፈተና አሰጣጡ በወረቀት እና በበይነ-መረብ /Online/ እንደሚሰጥ ታውቋል። በአሻግሬ ገ/ወልድ

Read More

ለሀገራችን ልማትና ዕድገት የሚረዳ ተዓማኒነት ያለዉ መረጃ ለማደራጀት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሚና ከፍተኛ ነው፦ አቶ በላይ ተሰማ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ የወሳኝ ኩነቶች ዘርፍ ከክልል ቢሮ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 ዕቅድ ዝግጅት የጋራ ምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት፤የክልሉ ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድነት አሸናፊ እንደተናገሩት፤ወሳኝ ኩነት ምዝገባ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ እና አስተዳደራዊ ዘርፍ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ…

Read More