asc
የክልሉ ጤና ቢሮ ለአመያ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ የሆስፒታሉን አገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማሻሻል እንደሆነም ተነግሯል። ድጋፉን ያስረከቡት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንደገለፁት ድጋፉ በሆስፒታሉ የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ ለማሳለጥ እና በፌዴራል መንግሥት የተጀመረው የህንፃ ዕድሳት ስራ…
