ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የንጹህ መጠጥ ተጠቃሚ የሚያደርገው የማጅ ቱም የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ በምዕራብ ኦሞ ዞን፣ በማጂ ቱም ከተማ አስተዳደር የተገነባው የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከ10ሺህ ለሚበልጡ የአከባቢው ነዋሪዎች አግልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቱ በባስኬት ፈንድ ፕሮግራም፤ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በውሃ ልማት ፈንድ በኩል በተገኘ 55 ከመቶ ብድር እና 45 በመቶ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የወጪ መጋራት ድርሻ የተገነባ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው 98…
