የሸካ ዞን ምክር ቤት 5ኛ ዙር፣ 13ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 24ኛ መደበኛ ጉባኤውን በቴፒ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
ጉባኤውን በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩት የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ካሳሁን ምክር ቤቱ በሕገ-መንግሥቱ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። ዞኑ አሁን ላይ ለሚገኝበት ዘላቂ ሠላም ምክር ቤቱ ጉልህ ሚና መጫወቱን ጠቅሰው ይህንንም አጽንቶ ለማስቀጠል ሁሉም የድርሻውን የመወጣት ኃላፊነት እንዳለበት አሳስበዋል። የዘንድሮው ጉባኤ 7ኛው ሀገራዊ…
