ሕዝቡ ለቢስት ባር በዓል አካባበር የሚያደርገዉ ንቅናቄና ተነሳሽነት አስደሳች ከመሆኑ ባሻገር የቤንች ብሔር ባህል ሳይበረዝ ተጠብቆ እንዲቆይ የወጣቶች ሚና ወሳኝ መሆኑን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ገለጹ፡፡
ምሁራኑም የቤንች ብሔር የዘመን መለወጫና ምስጋና በዓል ቢስት ባር ለሀገራችን ቱሪዝም ዕድገት የጎላ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል፡፡ በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህርና የ2024 የማንዴላ ዋሽግተን ፎሎዉ አሸናፊ ረዳት ፕሮፌሰር ታገል ወንድሙ እንዳስረዱት የቤንች ሕዝብ የራሱ የሆነ ማንነት ፣ ለየት ያለ የዳኝነት ሥነ-ሥርዓት ፣ የአመጋገብና የአለባበስ ሥርዓት ያለዉ ሁሉን አቃፊ ሕዝብ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በዚህም ብሔረሰቡ በዱም ሥርዓት የሚተዳደር…
