በዳዉሮ ዞን ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል በማኅጸን ውልቃት የሕክምና ዘርፍ እየተሰጠ የሚገኘው አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ እንዲሰጥ ለማድረግ የተቀናጀ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተገለጸ።
አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተግባሩ እየተመራ እንዳለም የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል። በዳዉሮ ዞን የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል በተለያዩ የሕክምና ዓይነቶች በሰለጠኑ ባለሙያዎች አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በተለይም በማህጸንና ጽንስ፣ በሕጻናት፣ በአጥንትና ድንገተኛ አደጋዎች፣ በአጠቃላይ ቀዶ ጥገናና በውስጥ ደዌ በሽታዎች በስፔሻሊት ደረጃ የሕክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል። ከእነዚህ አንዱ በሆነው በማኅጸንና…
