የደረሱ የማሽላ ሰብሎችን በወቅቱ በመሰብሰብ ከብክነት መታደግ እንደሚገባም የክልሉ ግብርና ቢሮ አሳስቧል ፡፡ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በበልግና በመኸር እንዲሁም በመስኖ ግብርና ስራዎች በሰብል ልማት በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ በክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታገል ገብሬ ተናግረዋል፡፡ በክልሉ በዋነኝነት ከሚለሙ ሰብሎች ማሽላ አንዱ መሆኑን የተናገሩት አቶ ታገል በቆላማና አርብቶ አደር አካባቢዎች…
