አመራሩ ያገኘውን ዕውቀትና ልምድ ወደተግባር በመቀየር ለህብረተሰቡ ለውጥ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ።
በኮንታ ዞን “የህልም ጉልበት፤ ለእመርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተጠናቋል። በማጠቃለያው መድረክ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ሰልጣኞች በነበራቸው ቆይታ በቂ ዕውቀትና ክህሎት ያገኙበት እንደሆነና የ3ኛ ዙር ስልጠና ካለፈው ዓመት ልምድ ተወስዶበት በተሻለ የቀረበበት እንደሆነ አስረድተዋል። የብልጽግና ፓርቲ…
