በዘንድሮ የመኸር ምርት ዘመን በክልሉ ከ391 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማልማት 17 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ይሰራል፡- አቶ ማስረሻ በላቸው
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የ2015/16 ዓ.ም የመኸር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2016/17 ዓ.ም የመኸር ንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በንቅናቄው መድረክ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው የልማት በክልላችን ግብርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሻሽሉ ተግባራት መከናወን በመቻላቸው ባለፉት ሁለት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ እምርታዊ ለውጥ እየመጣ ያለ…
