Trendings

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ቦንጋ ከተማ ገቡ

የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቦንጋ ከተማ ገብተዋል። ወደ ክልሉ ከገቡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች መካከል የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO)፣ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO)፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (OCHA) እና ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ይገኙበታል። የተባበሩት መንግስታት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ወደ…

Read More

በክልሉ የሚመረቱ የግብርና ውጤቶች ላይ እሴት ጨምሮ ለማገበያየት የሚያስችል ኢንዱስትሪ ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ።

የክልሉ ሦስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ ነው። ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማሳደግ ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ መተካትና ወደ ውጭ ለመላክ እየተደረገ ያለውን ጥረት ውጤታማ እያደረገ ነው ብለዋል። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እየተመረቱ ያሉ የግብርና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ከአካባቢ አልፎ በሀገር ደረጃና…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከዳውሮ ዞን ከተወጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ተወያዩ::

ርዕሰ መስተዳድሩ በዞኑ እየተከናወነ ባለውና በቀጣይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ነው ውይይት ያደረጉ። መንግስት ከሚሰራው የልማት ስራዎች ጎን ለጎን መላው የዞኑን ህዝብ በማስተባበር የዞኑን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ልሰራ እንደሚገባም አንስተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም ባለሀብቶችን በማስተባበርና ኢንቨስትመንትን በመጋበዝ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠር ትልቁ ተግባር ልሆን ይገባልም ብለዋል። በዞኑ ባለፉት አራትና አምስት የለውጥ አመታት በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ…

Read More

የቦንጋ ከተማ ኮሪደር ልማት አካል የሆነዉ የአረንጓዴ ፓርክ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገር እና የከተማዋን ገጽታ የሚቀይር ነው ሲሉ መምህራን ገለጹ

”ትውልድ በመምህራን ይቀረጻል፣ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሁሉም አከባቢ ከተወጣጡ ከትምህርት ቤት አመራሮች እና መምህራን ጋር የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል። የትምህርት ቤት አመራሮች እና መምህራን ከውይይት መድረኩ ጎን ለጎን በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና በርዕሰ መስተዳድር ዶክተር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ቅርብ ክትትል የተገነባዉ የቦንጋ ከተማ ኮሪደር ልማት አካል…

Read More

nvmn

የቤንች ሸኮ ዞን ገቢዎች መምሪያ ከስር መዋቅሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በበጀት አመቱ ዕቅድ አሰባሰብ ዙሪያ የምክክር መድረክ ተጠናቋል። በመድረኩ የተሳተፉ አካላት እንደተናገሩት የገቢ ሴክተር ከፍተኛ የሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ከሚስተዋልባቸው ተቋማት አንዱ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም መነሻ በዘርፉ የታክስ ማጭበርበርና ስወራ ፣ የግብር ከፋይ ቁጥር ቅሸባ ፣ ሀሰተኛ ደረሰኞች ማዘጋጀትን ጨምሮ በርካታ ወንጀሎች እየተፈጸሙ ይገኛሉ ብለዋል። በከተሞች…

Read More

ኤክስፖርትን በተመለከተ

እቅድ አሳካክታ የማታውቅ ሀገር በዚህ አመት 5.1 ቢሊዮን ዶላር ኤክስፖርት ለማድረግ አቅዳ ከ8.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያሳካች ሲሆን ከአቅድ ነው 3 ቢሊዮን ገደማ ጭማሪ ማግኘት የቻለች ሲሆን ከአምናው ከእጥፍ በላይ አሳክታለች፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ

Read More

የኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)::

የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ። በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ስራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል። ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራዎችን ለመፍጠር እንዳለመችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር…

Read More

ክልሉ ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተጠቆመ።

ከጅማ ታርጫ 800 መቶ ያስከፈለዉ አሽከርካሪ 5,000 ሺህ ብር ተቀጥቷል። አሽከርካሪዉ ከሌሊት 7:00 ሰዓት ተሳፋሪን በህገ ወጥ መንገድ ይዞ መንቀሳቀሱም ተገልጿል። መነሻዉን ጅማ መድረሻዉን ታርጫ ያደረገ ህዝብ ማመላለሻ ቅጥቅጥ ታርጋ 3_ኦሮ 65344 የሆነዉ ተሽከርካሪ ህጋዊ ታሪፍ 372 ብር ሆኖ እያለ ከአንድ መንገደኛ 800 ብር በማስከፈሉ በትራፊክ ተቆጣጣሪዎች መያዙንና ቅጣት መቀበሉ ተገልጿል። አሽከርካሪዉ ተቆጣጣሪዎች አይኖሩም በሚል…

Read More

የዓለም አቀፍና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች የሕዳሴ ግድብን ጎበኙ

የዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶችና ቀጣናዊ አጋር ድርጅቶች አመራሮች እንዲሁም የግድብ ደህንነት ባለሞያዎች የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጎብኝተዋል። በውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ አብርሃ አዱኛ (ዶ/ር) በተመራው የሕዳሴ ግድብ ጉብኝት መርሐ ግብር የተፋሰሱ ተጋሪ ሀገራት ኮሚሽነሮችና ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል። በተጨማሪም የካናዳና የአውስትራሊያ ግድቦች ማህበር፣ የኖርዌይ የሀይድሮፓወር ማህበር እንዲሁም የዛምቢያ ዛምቤዚ ወንዝ ባለስልጣን አመራሮች መሳተፋቸው ተገልጿል። የጉብኝት…

Read More

ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያሳየች ያለችው የላቀ ውጤትና እመርታ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያሳየች ያለችው የላቀ ውጤትና እመርታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ ገለፀ። በአየር መንገዱ ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነታ የራቁና ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑም ተጠቁሟል። በአሠራር ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች ቢኖሩ በጥብቅ ዲሲፕሊንና አሠራር የሚስተካከሉ መሆኑም ተመላክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሀገር ከፍታና የመልካም ገጽታ ማሳያነት የሚያስቀጥሉ ዘመናዊ አሠራሮች…

Read More