Trendings

የጋንዲዎች ተራራ ላይ ሀይቅ

የጋንዲዎች ተራራ ላይ ሀይቅ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በሸካ ዞን በአንድራቻ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከመድናችን አዲስ አበባ 700 ኪ.ሜ ከዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ በ35 ኪ.ሜ ላይ ይገኛል፡፡ በክልሉ ሸካ ዞን በአንድራቻ ወረዳ በዮክጭጪ ቀበሌ የሚገኝ ነዉ፡፡ ሀይቁ በተራራ ላይ ከመሆኑ በላይ ክብ ቅርጽ ያለዉ መሆኑና ዙሪያዉ ጥቅጥቅ ባለዉ ድንና በቀርከሃ የተከበበ መሆኑን፤ ክረምት ሆነ…

Read More

“ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ሃሳብ ሁለተኛው ዙር የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዘመቻ ተጀመረ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በቦንጋ ከተማ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድረግ ” በሚል መሪ ቃል ክልል አቀፍ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ዘመቻ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል። መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና የኢፌዲሪ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሚ በጋራ በመሆን ነው ። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ባደረጉት ንግግር የአካባቢያችን…

Read More

ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መረቁ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ በሚዛን አማን ከተማ የተገነባውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በይፋ መርቀው ከፍተዋል። በአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ፥ የኢፌዲሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አልማዝ መለሰን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ማዕከሉ ልዩ ልዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ውስጥ በመስጠት ቀልጣፋ የመንግሥት አግልግሎት ተደራሽ ለማድረግ…

Read More

የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብና መተንተን ወሳኝ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የራስን መረጃ በራስ አቅም መሰብሰብ እና መተንተን ወሳኝ ግብዓት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ”የመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነጻነት” በተሰኘውና ኢትዮጵያ በመረጃና በስታቲስቲክስ የሉዓላዊነት ጉዞ ያስመዘገበችውን ትልቅ ድል በተበሰረበት ሀገራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፤ በዘርፉ የተመለከቱት እመርታ እጅግ አስደሳች ሆኖ እንዳገኙት ገልጸዋል። መረጃ የዚህ ዘመን ስትራቴጂካዊ ሀብት…

Read More

በልማት ወደኋላ ለቀሩና ለተዘነጉ አካባቢዎች የብልፅግና ፓርቲ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጹ።

በዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲን የሚደግፍ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ስልፍ ተካሂዷል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ የብልፅግና ፓርቲ አካታች የፖለቲካ ምህዳር መፈጠሩ በመድረኩ የገለጹት። ፓርቲ ለዓመታት በልማት ተዘንግተውና ወደኋላ ቀርተው የኖሩ አካባቢዎችን ታሪክ በመቀየር የልማት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል!

6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ከደቂቃዎች በፊት ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ሌሎች የፌዴራል መንግስት ባለስልጣናትን ለጥያቄ የመጥራትና የሕግ አስፈጻሚውን አካል አሠራር የመመርመር ሥልጣን እንዳለው በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ 17 ተደንግጓል፡፡ በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከደቂቃዎች…

Read More

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በ3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት ተችሏል–የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ

በተጠናቀቀው የ2015 በጀት ዓመት በፍርድ ቤት ክርክር ከተደረገባቸው የወንጀል መዛግብቶች ውስጥ 3 ሺህ 943 መዛግብቶች ላይ ቅጣት ማሰጠት መቻሉን የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው የ2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የእውቅና መድረክ አካሂዷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተክሌ በዛብህ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፍትህ ስርዓቱን ለማሻሻል በርካታ የሪፎርም ስራዎች ተከናውነዋል።…

Read More

መገናኛ ብዙሃን ለብሔራዊ ጥቅም መከበርና ለዜጎች አብሮነት መጎልበት ያለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ ይገባል – አቶ መሀመድ እድሪስ

መገናኛ ብዙሃን ለብሔራዊ ጥቅም መከበርና ለዜጎች አብሮነት መጎልበት ያለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር መሀመድ እድሪስ ለኢዜአ እንዳሉት፤ መገናኛ ብዙሃን ለብሔራዊ ጥቅም መከበርና ለህዝብ አብሮነት መጠናከር ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ይህንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ከመገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅ መሆኑን አንስተው፤ በተቃራኒው አንዳንድ መገናኛ…

Read More

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በተደረገው ጥረት በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፦ ፈለቀች ተክለማሪየም (ዶ/ር)

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዞቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት አስተባባሪነት በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ በቦንጋ ከተማ ክልላዊ ማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ስራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ፕላን ቢሮ ምክትል ኃላፊ (ዶ/ር )ፈለቀች ተክለማርያም እንዳሉት ባለፋት የለውጥ ዓመታት ሴቶችን ማኅበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ገፅታ የቀየረ ዕምርታዊ…

Read More