የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ባለፋት ሶስት ቀናት ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቦንጋ ከተማ ስሰጥ የነበረው አመራር አቅም ግንባት ስልጠና ተጠናቀቀ።
“ከመልካም አመራርነት ወደ ታላቅ አመራርነት መሻገር ” በሚል መርህ ቃል ለክልሉ አመራሮች በተዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠና የክልሉ አጠቃላይ አመራር እንዲሁም የዞን፣ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደር አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል። ስልጠናው በአመራሩ ዘንድ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመፈጠር፤ አመራሩ በእያንዳንዱ ተግባር ላይ ፍጥነትና ፈጠራ በማከል ለክልሉ ሁለንተናዊ ለውጥ አስተዋጽኦ እንዲያበርክት የሚያዘጋጅ መኾኑን ነው ተሳታፊዎች የገለጹት። አመራሩ በስልጠናው ያገኘውን የጽንስ…
