በክልሉ በፌደራል መንግሥት የሚገነቡ የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክት ግንባታዎች ላይ የሚታየዉ የአፈጻጸም ችግር ሊታረም እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ወንድሙ ኩርታ አሳሰቡ
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከኢፌዲሪ ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አዲስ በተሻሻለው የካሳ አዋጅ ቁጥር 1336/2016 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና በክልሉ በፌደራል መንግሥት የሚገነቡ የመንገድ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃና የክልሉን ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ በክልሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተዋል። አዲስ ተሻሽለው የወጣዉ የካሳ አዋጅ ንብረት የመገመት፣ የመክፈል እና የማስነሳት ስራ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያግዝ…
የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች መብት፣ደህንነት፣ተሳትፎና ተጠቃሚነት ተረጋግጧል?
ሪፖርታጂ– አዘጋጅ ዕድገቱ በዛብህ ከጠቅላላው የአገራችን ህዝብ ከ80 በመቶ በላይ የሚሸፍነው ሴቶች ህጻናትና ወጣት የኀብረተሰብ ክፍል ሲሆን ይህም አሃዝ አገራችን ኢትዮጵያ አምራች ሃይል ያላት አገር መሆኗን ያመላክታል፡፡ በመሆኑም ዘላቂ ልማትና ቀጣይነት ያለው ዲሞክራሲ ለማረጋገጥ የሴቶች ህጻናትና የወጣቶች ተሳትፎ ማሳደግና ተጠቃሚነታቸው ማረጋገጥ ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ባለፉት አመታት ብሄራዊ የሴቶች ፖሊሲ ፤…
የቴፒ መለስተኛ የአውሮፕላን ማረፊያና የቡና ቅምሻ ማዕከል ተመረቅዉ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
የተመረቁት ፕሮጀክቶች የአካባቢውን ኢኮኖሚ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ፋይዳው የላቀ መሆኑም ተጠቁሟል። ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በምረቃዉ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዓመታት በቡና ሻይና ቅመማ ቅመም ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እየተገኘ ነው ብለዋል። በዞኑ ገበያ ተኮር የሆኑ እንደ ቡና፣ሻይና ቅመማ ቅመም ሰብሎች በስፋት የሚመረት ሲሆን የቡና ጥራት ሰርተፊኬሽን ማዕከሉ መመረቅ የተጀመረውን የብልጽግና…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ 7ኛውን ሀገራዊ ምርጫ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አፈጻጸምን በተመለከተ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ዶ/ር ነጋሽ ዋጌሾ ጋር ምክክር አደረገ፡፡
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲጠናቀቅ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን የጊዜ ሠሌዳ በማዘጋጀት ከክልሎች ጋር የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ እየገመገመ ይገኛል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብስቢ አቶ ተስፋዬ ንዋይ እና ሌሎች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስፈጻሚ አካላት በደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ተገኝተው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጋር የጋራ ምክክር አድርገዋል፡፡ የብሔራዊ ምርጫ…
ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ የታርጫ ከተማ ንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት መርቀው ከፈቱ።
ከ230 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ውጪ የተገነባው የታርጫ ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ፣ የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ እና ሌሎች የክልልና የፌዴራል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተኙበት ተመርቋል። ከተለያዩ ረጂ ተቋማት በተገኘው 170 ሚሊዮን ብር እና 1.142 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገነባው የውሃ…
የህብረት ሥራ ማህበራት የኦዲት አገልግሎት በብቃትና በጥራት ማከናወን ለማህበራት ደህንነት ጥበቃ ድርሻው የጎላ መሆኑን የክልሉ ህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ለዞንና ወረዳ የህብረት ሥራ ኦዲተሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በሚዛን አማን ከተማ እየሰጠ ይገኛል። የስልጠና መድረኩ ከካልም ፕሮግራም ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን ”በህብረት ሥራ ኦዲቲንግ እና በህብረት ሥራ ኦዲት አፈጻጸም መምሪያ ቁጥር 978/2016 ዙሪያ ያተኮረ ነው። በክልሉ የህብረት ሥራ ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ቀበሌ መንገሻ…
በክልሉ በሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ዘመናዊና ቀልጣፋ እንዲሆኑ ለማድረግና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ::
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ዲጂታል የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን በሚዛን አማን ከተማ በይፋ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማት ማናጅመንት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጫናቸው ወንድሙ እንደገለጹት በክልሉ ከሚገኙ ብዘሀ ከተሞች አንዷ በሆነችው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ዘመናዊ የማዘጋጃ ቤት የአገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋት…
ጥያቄዎች ሕጎችንና አሰራሮችን በመከተል ወንድማማችነትና አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እንዲያገኙ በትኩረት እንደሚሠራ ተገለጸ
የሚቀርቡ ጥያቄዎች ሕጎችንና አሰራሮችን በመከተል ወንድማማችነትና አንድነትን በሚያጠናክር አግባብ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እየሰጡ መሄድ ተጠናክሮ አንደሚቀጥል የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰንና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የማንነት፣ የአስተዳደር ወሰን የሰላም ግንባታ ቋሚ ጸሐፊ የተከበሩ አቶ ፍቅሬ አማን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ቋሚ ኮሚቴው በበጀት ዓመቱ በርካታ አንኳር ጉዳዮችን ማከናወኑን…
በዳዉሮ ዞን ታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል በማኅጸን ውልቃት የሕክምና ዘርፍ እየተሰጠ የሚገኘው አገልግሎት በተሻለ ሁኔታ እንዲሰጥ ለማድረግ የተቀናጀ ርብርብ እንደሚጠይቅ ተገለጸ።
አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ተግባሩ እየተመራ እንዳለም የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል። በዳዉሮ ዞን የታርጫ ጠቅላላ ሆስፒታል በተለያዩ የሕክምና ዓይነቶች በሰለጠኑ ባለሙያዎች አገልግሎቱን ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። በተለይም በማህጸንና ጽንስ፣ በሕጻናት፣ በአጥንትና ድንገተኛ አደጋዎች፣ በአጠቃላይ ቀዶ ጥገናና በውስጥ ደዌ በሽታዎች በስፔሻሊት ደረጃ የሕክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል። ከእነዚህ አንዱ በሆነው በማኅጸንና…
