የተጀመረው የሚዲያ የመስክ ምልከታ እውነታን ለህዝብ ገልጦ ለማሳየት ዕድል የሚሰጥ ነው ሲሉ የሚዲያ ባለሙያዎች ተናገሩ።
ባለሙያዎቹ ይህን ያሉት በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ እየለማ የሚገኘውን የበልግ እርሻ የመስክ ምልከታ ባደረጉበት ወቅት ነው። በክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባዘጋጀው የሚዲያ መስክ ምልከታ ሀገር አቀፍና የክልል ሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ። ከተሳተፉት ሚዲያዎች መካከል ጋዜጠኛ ቀደሰ ተክሌ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የመጡ ሲሆን እየተከናወነ ያለው የበልግ እርሻ አርሶአደሮችን ራሳቸውን ለመለወጥ የሚያደርጉትን ጥረት ይበልጥ አጉልቶ…
