የብራዚል አውሮፕላን አምራች ኩባንያ በኢትዮጵያ መሥራት እንደሚፈልግ ገለፀ
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶ/ር ዓለሙ ስሜ የብራዚል ምክትል አምባሳደር ጃክሰን ሊማን ጨምሮ ኢምብሬር የተባለው የሀገሪቱ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ የስራ ኃላፊዎችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። መንግሥት ለአቪዬሽን ዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ አንስተዋል። በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከዓለም ጋር በማገናኘት የአህጉሪቱ ኩራት ሆኖ እንዲዘልቅ ማድረግ ተችሏል ብለዋል። በአቪዬሽን ዘርፍ የተሰማሩ…
