በበጀት ዓመቱ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች 30 ሚሊዮን ዜጎችን ለማመካከር እቅድ ይዞ እየሠራ እንደሚገኝ የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በሚዛን አማን ከተማ በማህበረሰብ ተኮር ምክክር ዉጤታማነት ዙሪያ በሠላም ሚኒስቴር አማካይነት ለተከታታይ ሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየዉ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቋል። በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከ6ቱም ዞኖች ለተወጣጡ የሠላምና ጸጥታ ተቋም ባለሙያዎችና የማህበረሰብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሙያተኞች የአመቻችነት ሥልጠና እንዲወስዱ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ ተግባራት ውጤታማነት ዙሪያም አቅጣጫ ተቀምጧል። የሥልጠናው ተሳትፊዎች በቆይታቸው በቂ…
