Trendings

በ118 ሚለየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሰንገጢ- ጩርጩራ የመንገድ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ

በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ የተገነባውን የሰንገጢ -ጩርጩራ የመንገድ ፕሮጀክትተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነዋል። 40 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው በዳውሮ ዞን ኢሳራ ወረዳ የተገነባውን የሰንገጢ ጩርጩራ መንገድ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) መርቀው ከፍተዋል። መንገዱ የተገነባው ከክልሉ መንግስት በተመደበው 83 ሚለየን ብር እና የዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ በተመደበው 35 ሚለየን…

Read More

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የመማር ማስተማር ሂደት ተጎበኘ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያለውን የመማር ማስተማር እና የተግባር ማሰልጠኛ ክፍሎችን ጎብኝተዋል። ኮሌጁ ተማሪዎች ወደ ሥራ ከመሰማራታቸው በፊት በቂ ክህሎት እንዲጨብጡ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገልጿል። ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት የንድፈ-ሀሳብ ትምህርቱን ከተግባር ጋር ማቀናጀቱ ለጤናው ዘርፍ ዕድገት ወሳኝ መሆኑ ተመልክቷል። የመማር…

Read More

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በክልሉ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በክልሉ የልምድ ልውውጥ እያደረጉ ይገኛሉ የ ከተማ አስተዳደሩ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) ሠራተኞችና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላተ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች በፕሮግራሙ የተሰሩ ስራዎች የልምድ ልውውጥ የመስክ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። የጉብኝቱ ዓላማ በክልሉ ግብርና ቢሮ የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም (FSRP) የተከናወኑ ውጤታማ አፈጻጸሞች…

Read More

የኢትዮጵያ የብሪክስ ብሔራዊ የሚኒስትሮች አስተባባሪ ኮሚቴ ሁለተኛ ስብሰባውን አካሄደ

የኢትዮጵያ የብሪክስ ብሔራዊ የሚኒስትሮች አስተባባሪ ኮሚቴ ሁለተኛ ስብሰባውን ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም አካሂዷል። የስብሰባው ዓላማ ኢትዮጵያ በብሪክስ ስብስብ ውስጥ ያላትን ተሳትፎ መገምገም እና ቀጣይ ስራዎች ላይ አቅጣጫ ማስቀመጥ መሆኑም ተገልጿል። የኮሚቴው ሰብሳቢና የኢትዮጵያ የብሪክስ ብሔራዊ ተወካይ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ፤ ኢትዮጵያ በብሪክስ እንቅስቃሴዎች ላይ የምታደርገው ንቁ እንቅስቃሴ ለኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጥቅሞች፣ ለሀገራዊ ልማት…

Read More

ምክር ቤቱ አራት ስምምነቶችን አጸደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 29ኛ መደበኛ ስብሰባው አራት የስምምነት አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል። በቀዳሚነት የጸደቀው ለአካባቢ እና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት በኢትዮጵያ እና በጣሊያን መንግስት መካከል የተደረገው የ11 ሚሊየን 500 ሺህ ዩሮ የብድር ስምምነት ነው። ለመማር ማስተማር ማጎልበቻ የትምህርት ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር ያደረገው…

Read More

ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ይሳተፋሉ

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ23 ሚሊየን በላይ ዜጎች ይሳተፋሉ አለ፡፡ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቱ 14 መርሐ ግብሮች እንዳሉት በሚኒስቴሩ የወጣቶች ብሔራዊ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስፋፊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዐቢይ ኃ/መለኮት ተናግረዋል። የዳበረ የመደጋገፍ ዕሴትን ለማሳደግ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የላቀ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎን በማሳደግ አሠራሩን…

Read More

“በጎነት ለጤንነት” በሚል መሪ ቃል የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ነፃ የህክምና አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራም በካፋ ዞን ገብረ ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ተካሂዷል።

የ2016 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እና የካፋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አክሊሉ አሰፋ በይፋ አስጀምሯል። የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም እንዳሉት” በጎነት ለጤንነት” በሚል መሪ ቃል ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የነፃ ምርመራና ህክምና…

Read More

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓም የክረምት ወራት በጎ አገልግሎት አፈጻጸም ግምገማ ማካሄድ ጀመረ፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2016 ዓም የክረምት ወራት በጎ አገልግሎት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ባሻ እንደገለጹት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ሁለንተናዊ ብልጽግና…

Read More

ባለፉት ጊዜያት የተተከሉ ችግኞች የተሻለ የጽድቀት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ግብርና አካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ ጽ/ቤት አስታወቀ

በከተማ አስተዳደሩ የሚዲያ አካላት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ከመትከል ባሻገር የተተከሉትንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል። ሀገር አቀፍና ክልላዊ የሚዲያ ተቋማት በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል ። የሚዲያ አካላት በከተማ አስተዳደሩ ጋቡቃ መንደር በመገኘት ችግኝ የመትከልና በጽድቀት ላይ የሚገኙትን ምልከታ አድርገዋል። በምልከታው ወቅት ከ2014_2016 ዓ/ም ድረስ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎች ተጠናክረው…

Read More

የኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)::

የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ። በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ስራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል። ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራዎችን ለመፍጠር እንዳለመችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር…

Read More