በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም የ3 ጊዜ የሞት ፍርደኛ እንደነበር ፖሊስ አስታወቀ
ሰሞኑን በአቪዬሽን አሰራር ጥሰት ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ፣ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1999 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ “ዳዊት ድሪባ በዳኔ” በሚል ስም 3 ጊዜ የሞት ፍርድ ተፈርዶበት እንደነበር ፖሊስ ገልጿል፡፡ ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ እንደተቻለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታሕሳስ 25 ቀን 1999…
