Trendings

ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢቢሲ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዋና ስራ-አስፈፃሚና ከሌሎች የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በክልሉና በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መካከል ያለውን ግንኝነት ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ። ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኢቢሲ ህዝብና መንግሥትን በማቀራረብ እንዲሁም ከህዝብ የሚነሱ ጥያቄዎችን ሚዛናዊ…

Read More

“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልፅግና!”

“ቃልን በተግባር ለኢትዮጵያ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ አባላት ኮንፈረንስ ከመሠረታዊ ድርጅት እስከ ክልል ከመጋቢት 8-14 /2016 ዓ.ም ድረስ ይካሄዳል። በክልል በሁሉም ዞን ፣ወረዳ ፣ከተማ እና ቀበሌ /መሠረታዊ ድርጅት እንዲሁም በክልል ማዕከል የማጠቃለያ ፣ የተሳካ፣ ደማቅ እና በዓይነቱ ልዩ የሆነ የአባላት ኮንፈረንስ ለማድረግ የቅድመ-ዝግጅት ስራ የተሰራ ይገኛል። ፓርቲያችን በስድስተኛው…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበረከቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዛሬ በአድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለአምስት ተቋማት ‘የኢትዮጵያ ተቋማት ስኬት ሽልማትን’ አበርክተዋል። በሽልማቱ የከበሩት ተቋማት የግብርና ሚኒስቴር/በስንዴ ልማት ፕሮግራም/፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት፣ ኢትዮ ቴሌኮም እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት መሆናቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ተቋማቱ የኢትዮጵያ የእድገት እና የፈጠራ ልክ ማሳያ…

Read More

የክልሉ የስፖርት ፌዴሬሽኖች የሚያደርገው የጋራ ውይይት መድረክ በታርጫ ከተማ ተካሄደ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ከክልሉ የስፖርት ፌዴሬሽኖች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል። በመድረኩ የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ አመራሮች፣ የክልሉ ስፖርት ፌዴሬሽኖች ፕረዚዳንቶችና ምክትል ፕረዚዳንቶች፣ የባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊዎች፣ የዞን ፋሲሊቲና አደረጃጀት ሥራ ሂደት ቡድን መሪዎች፣ የቢሮ የስፖርት ዘርፍ ዳይሬክተሮች፣ ባለሙያዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል። የምክክር መድረኩ…

Read More

በክልሉ በመደማመጥ፣ በመከባበርና በመመካከር የተረጋጋ የፖለቲካ ስነ- ምህደር መፍጠር መቻሉን ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ገለጹ

የፌዴራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ከወከላቸው ህዝብ ጋር ያደረጉት የውይይት ግብረ-መልስ ለክልሉ ካቢኔ አካላት በቦንጋ ከተማ አቅርበዋል። በመድረኩ በክልሉ የተጀመሩ የሠላምና ፀጥታ ንቅናቄ መድረኮች ውጤታማ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ተመልክቷል ፡፡ በክልሉ የጤናና የውሃ ፕሮጀክቶችን ለማንቀሳቀስ እና በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ለመጨረስ የሚደረገው ጥረት እጅግ አበረታች መሆኑ ተገልጿል፡፡ የተጀመሩ የተለያዩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም…

Read More

ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን እየጎበኙ ነው

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ የሚገኘውን የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካን እየጎበኙ ነው፡፡ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) እና ሌሎች የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በጉብኝቱ እየተሳተፉ ነው ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል፡፡

Read More

የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ ከዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

የግብርና ሚኒስትር ዶክተር ግርማ አመንቴ ከዓለም ባንክ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ፍሎሪበርት ንጋሩኮ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሚኒስትሩ መንግስት ባለፉት 5 ዓመታት ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ ትኩረት በመስጠት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዓለም ባንክ የበጀት ድጋፍ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በመተግበር ላይ መሆናቸውን ገልጸው፤ ባንኩ ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ጥረት ይበልጥ እንዲያግዝ ጠይቀዋል፡፡ ዶክተር…

Read More

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች እና የጋምቤላ ክልሎች በሰላም ግንባታ ዙሪያ ተወያዩ

የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ በሁለቱ ክልል የሚገኙ አዋሳኝ ዞኖችና ወረዳዎች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች በጋራ በውይይትና በምክክር በመፍታት ቀጠናው የተረጋጋና የልማት አካባቢ ለማድረግ የታሰበ ነው :: ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀጠናው አልፎ አልፎ የሚስተዋለውን የግድያና ዝርፊያ ችግር ጥቅት ፀረ ሰላም ሃይሎችና ሽፍቶች የሚፈጥሩት ችግር እንደሆነና ሰፊውን ህዝብ እንደማይወክል ታውቆ ሰላማዊና አጥፊ ሰዎችን በመለየት ችግር ፈጣሪዎችን ብቻ ተከታትሎ…

Read More

ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያሳየች ያለችው የላቀ ውጤትና እመርታ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ኢትዮጵያ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ እያሳየች ያለችው የላቀ ውጤትና እመርታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ፋሲሊቲ ኮሚቴ ገለፀ። በአየር መንገዱ ላይ በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚሰነዘሩ አሉባልታዎችና የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ከእውነታ የራቁና ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑም ተጠቁሟል። በአሠራር ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች ቢኖሩ በጥብቅ ዲሲፕሊንና አሠራር የሚስተካከሉ መሆኑም ተመላክቷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድን የሀገር ከፍታና የመልካም ገጽታ ማሳያነት የሚያስቀጥሉ ዘመናዊ አሠራሮች…

Read More

1445ኛው የረመዳን ወር ፆም ነገ ይጀመራል

1445ኛው የረመዳን ወር ፆም ነገ ሰኞ መጋቢት 2 እንደሚጀመር የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታውቋል። የሳኡዲ አረቢያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች በተተከሉ አስራ አንድ አስትሮኖሚ ማዕከሎችን መሰረት በማድረግ ባሰባሰበው መረጃ ጨረቃ መታየቷ አሳውቋል። ይህንን ተከትሎም የረመዳን ፆም ነገ ሰኞ እንደሚጀመር ይፋ አድርጓል። ታላቁን የረመዳን ወር በመተሳሰብና አላህን በመለመን ማሳለፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች…

Read More