የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው የላቀ አበርክቶ አድርገዋል – ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ ቀኑን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ሴቶች ለሀገራቸው ነፃነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ማህበራዊ እሴቶችና ባህሎችን ለማፅናት ያበረከቱት አስተዋጽኦ የላቀ ነው ብለዋል። እንቅፋቶችንና ጎታች እሳቤዎችን በመጣል፣ በመላ አቅማቸው የኢትዮጵያን የመዘመን መንገድ ዋነኛ መሪና ተዋናይ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ዘንድሮ ቀኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ…
