ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የኦሮምያ ክልል ርዕሰመስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ ጋር በአምቦ ወረዳ በነበራቸው ጉብኝት የኬኛ ቤቭሬጅ ፋብሪካን ተመልክተዋል። ፋብሪካው በመጪዎቹ ሶስት ሳምንታት ውስጥ ወደሥራ የሚገባ ሲሆን 3 ሚሊዮን ሄክቶሊትር የማምረት አቅምም አለው።
የአስተዳደር ሥራን ወደ ሕዝብ ለማቅረብ የቀበሌዎች መጠናከር ወሳኝ ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በየአካባቢው ለሕዝብ ቅርብ የሆነ አስተዳደር ለመፍጠር (power devolution) ጥረት እያደረገ ነው። ከዚህ አንጻር በአምቦ ወረዳ የአንድ ቀበሌ እንቅስቃሴ በጉብኝት ወቅት ታይቷል። በዚህ ቀበሌን የማብቃት ተግባር በክልሉ 7342 ቀበሌዎች ተደራጅተዋል። 50,000 የሰው ኃይል ተመድቦላቸዋል። ከዚህ ቀደም በወረዳዎች ተማክለው የነበሩ ሞያዊና አስተዳደራዊ አገልግሎቶች በቀበሌ ደረጃ…
